የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?

ምን ትላለህ?

  • አዎ

  • አይ

  • እኔ እንጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን [ይመጣል]።” (2 ጢሞቴዎስ 3:1) የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢትና በዓለም ላይ የሚታዩት ክስተቶች የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ጦርነት፣ ረሃብ፣ የምድር ነውጥና ገዳይ በሽታዎች የመጨረሻዎቹ ቀናት ምልክቶች ናቸው።—ማቴዎስ 24:3, 7፤ ሉቃስ 21:11

  • በመጨረሻዎቹ ቀናት የሰው ልጆች ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ሁኔታ በእጅጉ ያሽቆለቁላል።—2 ጢሞቴዎስ 3:2-5

የሰው ልጆች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?

ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ? አንዳንዶች በመጨረሻዎቹ ቀናት ማብቂያ ላይ ምድርና በውስጧ ያሉ ነገሮች በሙሉ ይጠፋሉ ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ተስፋ ያደርጋሉ። አንተስ ምን ብለህ ታምናለህ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”መዝሙር 37:29

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?