በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

አንደኛ ዜና መዋዕል 20:1-8

የመጽሐፉ ይዘት

  • ራባ ተያዘች (1-3)

  • ግዙፍ የሆኑት ፍልስጤማውያን ተገደሉ (4-8)

20  በዓመቱ መባቻ፣* ነገሥታት ለውጊያ በሚዘምቱበት ወቅት ኢዮዓብ+ የጦር ሠራዊቱን በመምራት የአሞናውያንን ምድር አወደመ፤ ወደ ራባ+ ሄዶም ከበባት፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።+ ኢዮዓብም በራባ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አፈራረሳት።+  ከዚያም ዳዊት የማልካምን* ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት* ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+  ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው።+ ዳዊት በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።  ከዚህ በኋላ ከፍልስጤማውያን ጋር በጌዜር ጦርነት ተከፈተ። በዚህ ጊዜ ሁሻዊው ሲበካይ+ የረፋይም+ ዘር የሆነውን ሲፓይን* ገደለው፤ ፍልስጤማውያንም ድል ተመቱ።  ዳግመኛም ከፍልስጤማውያን ጋር ጦርነት ተካሄደ፤ የያኢር ልጅ ኤልሃናን የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ዘንግ ያለው ጦር ይዞ የነበረውን የጎልያድን+ ወንድም ጌታዊውን ላህሚን ገደለው።  እንደገናም በጌት+ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ በዚያም በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች፣ በድምሩ 24 ጣቶች ያሉት በጣም ግዙፍ የሆነ ሰው ነበር፤+ እሱም የረፋይም ዘር+ ነበር።  ይህ ሰው እስራኤልን ይገዳደር+ ስለነበር የዳዊት ወንድም የሺምአ+ ልጅ ዮናታን ገደለው።  እነዚህ በጌት+ የሚኖሩ የረፋይም+ ዘሮች ነበሩ፤ እነሱም በዳዊት እጅና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

የበልግን ወቅት ያመለክታል።
ይህ የአሞናውያን ጣዖት ሳይሆን አይቀርም፤ በሌላ ቦታ ላይ ሞሎክ ወይም ሚልኮም ተብሎም ተጠርቷል።
አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
በ2ሳሙ 21:18 ላይ ሳፍ ተብሎም ተጠርቷል።