በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

አንደኛ ዜና መዋዕል 1:1-54

የመጽሐፉ ይዘት

  • ከአዳም እስከ አብርሃም (1-27)

  • የአብርሃም ዘሮች (28-37)

  • ኤዶማውያን፣ ነገሥታታቸውና አለቆቻቸው (38-54)

1  አዳም፣ሴት፣+ሄኖስ፣  ቃይናን፣መላልኤል፣ያሬድ፣+  ሄኖክ፣+ማቱሳላ፣ላሜህ፣  ኖኅ፣+ሴም፣+ ካምና ያፌት።+  የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣+ መሼቅ+ እና ቲራስ+ ነበሩ።  የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣ ሪፋት እና ቶጋርማ+ ነበሩ።  የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም እና ሮዳኒም ነበሩ።  የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣+ ሚጽራይም፣ ፑጥ እና ከነአን+ ነበሩ።  የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣+ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ እና ሳብተካ ነበሩ። የራአማ+ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ። 10  ኩሽ ናምሩድን+ ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። 11  ሚጽራይም ሉድን፣+ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣+ 12  ጳትሩሲምን፣+ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን+ የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን+ ወለደ። 13  ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ 14  እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣+ 15  ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ 16  አርዋዳዊውን፣+ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን ወለደ። 17  የሴም ወንዶች ልጆች ኤላም፣+ አሹር፣+ አርፋክስድ፣ ሉድ እና አራምእንዲሁም* ዑጽ፣ ሁል፣ ጌተር እና ማሽ+ ነበሩ። 18  አርፋክስድ ሴሎምን+ ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ። 19  ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ*+ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ* ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን ነበር። 20  ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣+ 21  ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ 22  ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ 23  ኦፊርን፣+ ሃዊላን+ እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ። 24  ሴም፣አርፋክስድ፣ሴሎም፣ 25  ኤቤር፣ፋሌቅ፣+ረኡ፣+ 26  ሴሮህ፣+ናኮር፣+ታራ፣+ 27  አብራም ማለትም አብርሃም።+ 28  የአብርሃም ወንዶች ልጆች ይስሐቅ+ እና እስማኤል+ ነበሩ። 29  የቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው የሚከተለው ነው፦ የእስማኤል የበኩር ልጅ ነባዮት+ ከዚያም ቄዳር፣+ አድበዔል፣ ሚብሳም፣+ 30  ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ ሃዳድ፣ ቴማ፣ 31  የጡር፣ ናፊሽ እና ቄድማ። እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ነበሩ። 32  የአብርሃም ቁባት የነበረችው ኬጡራ+ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዚምራን፣ ዮቅሻን፣ ሚዳን፣ ምድያም፣+ ይሽባቅ እና ሹሃ+ ነበሩ። የዮቅሻን ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ። 33  የምድያም ወንዶች ልጆች ኤፋ፣+ ኤፌር፣ ሃኖክ፣ አቢዳዕ እና ኤልዳዓ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 34  አብርሃም ይስሐቅን+ ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች ኤሳው+ እና እስራኤል+ ነበሩ። 35  የኤሳው ወንዶች ልጆች ኤሊፋዝ፣ ረኡዔል፣ የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ+ ነበሩ። 36  የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማን፣+ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም፣ ቀናዝ፣ ቲምና እና አማሌቅ+ ነበሩ። 37  የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ+ ነበሩ። 38  የሴይር+ ወንዶች ልጆች ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣ ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን+ ነበሩ። 39  የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሆማም ነበሩ። የሎጣን እህት ቲምና+ ትባል ነበር። 40  የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ነበሩ። የጺብኦን ወንዶች ልጆች አያ እና አና+ ነበሩ። 41  የአና ልጅ* ዲሾን ነበር። የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን+ ነበሩ። 42  የኤጼር+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ነበሩ። የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን+ ነበሩ። 43  እነዚህ በእስራኤላውያን*+ ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት በኤዶም+ ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው፦ የቢዖር ልጅ ቤላ፣ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 44  ቤላ ሲሞት የቦስራው+ የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 45  ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 46  ሁሻም ሲሞት ምድያምን በሞዓብ ምድር* ድል ያደረገው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም አዊት ይባል ነበር። 47  ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 48  ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 49  ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 50  ባአልሀናን ሲሞት ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማውም ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት። 51  ከዚያም ሃዳድ ሞተ። የኤዶም አለቆች፣* አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣+ 52  አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣ 53   አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ 54  አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም ነበሩ። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቀጥሎ የተዘረዘሩት የአራም ወንዶች ልጆች ናቸው። ዘፍ 10:23ን ተመልከት።
“ክፍፍል” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “የምድር ሕዝብ ተከፋፍሎ።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “በእስራኤል ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ሜዳ።”
ቃል በቃል “ሺኮች።” የነገድ አለቃ የሆነ ሰው “ሺክ” ተብሎ ይጠራ ነበር።