በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ዮናስ 2:1-10

የመጽሐፉ ይዘት

  • ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ጸለየ (1-9)

  • ዓሣው ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው (10)

2  ከዚያም ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ ጸለየ፤+  እንዲህም አለ፦ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ይሖዋ ተጣራሁ፤ እሱም መለሰልኝ።+ በመቃብር* ጥልቅ* ውስጥ ሆኜ እርዳታ ለማግኘት ጮኽኩ።+ አንተም ድምፄን ሰማህ።   ወደ ጥልቁ፣ ወደ ታችኛው የባሕሩ ወለል በጣልከኝ ጊዜፈሳሹ ውኃ ዋጠኝ።+ ማዕበሎችህና ሞገዶችህ ሁሉ በላዬ አለፉ።+   እኔም ‘ከፊትህ አባረርከኝ! ቅዱስ የሆነውን ቤተ መቅደስህን ዳግመኛ እንዴት መመልከት እችላለሁ?’ አልኩ።   ውኃው ዋጠኝ፤ ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጣለው፤*+ጥልቁ ውኃ ከበበኝ። የባሕር አረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ።   ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥኩ። የምድር መቀርቀሪያዎች ለዘላለም ተዘጉብኝ። ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓዱ ውስጥ አወጣህ።+   ሕይወቴ* እየተዳከመች ስትሄድ ይሖዋን አስታወስኩ።+ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ ገባ።+   ለማይረቡ ጣዖቶች ያደሩ ሰዎች ታማኝ ፍቅር የሚያሳያቸውን ይተዋሉ።*   እኔ ግን በምስጋና ድምፅ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ። የተሳልኩትን እከፍላለሁ።+ መዳን ከይሖዋ ነው።”+ 10  በኋላም ይሖዋ ዓሣውን አዘዘው፤ ዓሣውም ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ሆድ።”
ወይም “ውኃው እስከ ነፍሴ ድረስ ሸፈነኝ።”
ወይም “ነፍሴ።”
“ታማኝነታቸውን ይተዋሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።