በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ዘካርያስ 3:1-10

የመጽሐፉ ይዘት

  • ራእይ 4፦ ሊቀ ካህናቱ ልብስ ተቀየረለት (1-10)

    • ሰይጣን ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን ተቃወመው (1)

    • “ቀንበጥ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!” (8)

3  እሱም ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን+ በይሖዋ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፤ ሰይጣንም+ እሱን ለመቃወም በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።  ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤+ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው+ ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?”  ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር።  መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን “ያደፈውን ልብሱን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም እሱን “እነሆ፣ ጥፋትህን* አስወግጄልሃለሁ፤ ደግሞም ጥሩ ልብስ ትለብሳለህ”*+ አለው።  እኔም “በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም ይደረግለት”+ አልኩ። እነሱም ንጹሑን ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት፤ የይሖዋም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።  ከዚያም የይሖዋ መልአክ ኢያሱን እንዲህ አለው፦  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመንገዶቼ ብትመላለስና በፊቴ ኃላፊነቶችህን ብትወጣ፣ በቤቴ ፈራጅ ሆነህ ታገለግላለህ፤+ ቅጥር ግቢዎቼንም ትንከባከባለህ፤* እኔም እዚህ በቆሙት መካከል በነፃነት የመቅረብ መብት እሰጥሃለሁ።’  “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+  በኢያሱ ፊት ያስቀመጥኩትን ድንጋይ እዩ! በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እኔም በላዩ ላይ ጽሑፍ እቀርጻለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።’+ 10  “‘በዚያ ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘እያንዳንዳችሁ ጎረቤታችሁን ከወይናችሁና ከበለስ ዛፋችሁ ሥር እንዲቀመጥ ትጋብዛላችሁ።’”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እነሆ፣ በደልህን።”
ወይም “የክት ልብስ ትለብሳለህ።”
ወይም “በቅጥር ግቢዎቼ ላይ ኃላፊ ትሆናለህ፤ ትጠብቃለህ።”