በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ዘሌዋውያን 3:1-17

የመጽሐፉ ይዘት

  • የኅብረት መሥዋዕት ተደርጎ የሚቀርብ መባ (1-17)

    • ስብ ወይም ደም አትብሉ (17)

3  “‘አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የኅብረት መሥዋዕት*+ ቢሆንና ከከብቶች መካከል ወስዶ የሚያቀርብ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል።  እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይታረዳል፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል።  እሱም ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤+ ይኸውም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣+ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣  ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል።+  የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ ላይ ያጨሱታል፤+ ይህም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።+  “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው መባ ከመንጋው መካከል የተወሰደ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን ያቀርባል።+  የበግ ጠቦት መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል።  እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ለፊት ይታረዳል። የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል።  ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይም ስቡን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል።+ ከጀርባ አጥንቱ አጠገብ ያለውን ላት በሙሉ፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ ያነሳዋል፤ 10  ደግሞም ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያነሳዋል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ 11  ካህኑም እንደ ምግብ* ይኸውም ለይሖዋ በእሳት እንደሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ 12  “‘ፍየል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። 13  እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፤ በመገናኛ ድንኳኑም ፊት ይታረዳል፤ የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። 14  ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርበውም እነዚህን ነው፦ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣+ 15  ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። 16  ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው።+ 17  “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የሰላም መባ መሥዋዕት።”
ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”
ቃል በቃል “ዳቦ።” እንደ አምላክ ድርሻ የሚቆጠረውን የኅብረት መሥዋዕት ያመለክታል።
ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”