በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ኤርምያስ 5:1-31

የመጽሐፉ ይዘት

  • ሕዝቡ የይሖዋን ተግሣጽ አልሰማም (1-13)

  • ጥፋት ቢደርስባቸውም ሙሉ በሙሉ አልጠፉም (14-19)

  • ይሖዋ ሕዝቡን ተጠያቂ አደረገ (20-31)

5  በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ። ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ። ፍትሕን የሚያደርግ፣+ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነበአደባባዮቿ ፈልጉ፤እኔም ይቅር እላታለሁ።   “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+   ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+ አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።* አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+ ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤+ለመመለስም አሻፈረን አሉ።+   እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው። የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸውየሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።   ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድአስተውለው መሆን አለበትና።+ ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤ማሰሪያውንም በጥሰዋል።”   ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል። ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል። በደላቸው በዝቷልና፤የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+   ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ? ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+ እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ።   እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+   “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+ 10  “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+ የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤የይሖዋ አይደሉምና። 11  የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤትበእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+ 12  “እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም።*+ በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+ 13  ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤ቃሉም* በውስጣቸው የለም። ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!” 14  ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤+እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤እሳቱም ይበላቸዋል።”+ 15  “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። “እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው። ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣ቋንቋውን የማታውቀውናንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+ 16  የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው። 17  እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ። መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ። የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ። የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።” 18  “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+ 19  ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+ 20  ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦ 21  “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+ ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤+ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም።+ 22  ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም? ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌአሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ። ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+ 23  ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+ 24  እነሱም በልባቸው “እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብበወቅቱ የሚሰጠንን፣የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንንአምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+ 25  የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+ 26  በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና። አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ። ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ። ሰዎችን ያጠምዳሉ። 27  በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+ ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው። 28  ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤በክፋት ተሞልተዋል። ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡአባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+ 29  “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም? 30  በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦ 31  ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ። የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+ ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “እነሱ ግን አልደከሙም።”
ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”
“እሱ የለም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
የአምላክን ቃል ያመለክታል።
ቃል በቃል “ልብ የሚጎድላችሁ ሞኞች።”
ወይም “ነፍሴ ልትበቀል።”