በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ኤርምያስ 49:1-39

የመጽሐፉ ይዘት

  • በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-6)

  • በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (7-22)

    • ኤዶም ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳለች (17, 18)

  • በደማስቆ ላይ የተነገረ ትንቢት (23-27)

  • በቄዳርና በሃጾር ላይ የተነገረ ትንቢት (28-33)

  • በኤላም ላይ የተነገረ ትንቢት (34-39)

49  ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም? ወራሽስ የለውም? ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+ ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”   “‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ+ ላይየጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ* የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤በእሷም ሥር* ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’ ‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’+ ይላል ይሖዋ።   ‘ሃሽቦን ሆይ፣ ጋይ ስለወደመች ዋይ ዋይ በዪ! በራባ ሥር ያላችሁ ከተሞች ሆይ፣ ጩኹ። ማቅ ልበሱ። ማልካም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበግዞት ስለሚወሰድ+ከድንጋይ በተሠራ የእንስሳት ማጎሪያ* ውስጥ ወዲያ ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ።   አንቺ በውድ ሀብቶችሽ የምትታመኚ፣“ማን ይነካኛል?” የምትዪከዳተኛ የሆንሽ ሴት ልጅ ሆይ፣በሸለቆዎችሽ* ይኸውም ውኃ በሚንዶለዶልበት ሜዳሽ የምትኩራሪው ለምንድን ነው?’”   “‘እነሆ፣ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ፣በአንቺ ላይ የሚያስፈራ ነገር አመጣለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ። ‘እናንተም በየአቅጣጫው ትበታተናላችሁ፤የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።’”   “‘ከዚያ በኋላ ግን ተማርከው የተወሰዱትን አሞናውያንን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።”  የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ “ጥበብ ከቴማን+ ጠፍቷል? ጥሩ ምክርስ ከአስተዋዮች ጠፍቷል? ጥበባቸውስ ተበላሽቷል?   የዴዳን+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ሽሹ! ወደ ኋላ ተመለሱ! ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ! ትኩረቴን ወደ እሱ በማዞርበት ጊዜበኤሳው ላይ ጥፋት አመጣለሁና።   ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም? ሌቦች በሌሊት ቢመጡ፣የሚዘርፉት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ነው።+ 10  እኔ ግን ኤሳውን እርቃኑን አስቀረዋለሁ። መደበቅ እንዳይችልመሸሸጊያ ቦታዎቹን እገልጣለሁ። ልጆቹ፣ ወንድሞቹና ጎረቤቶቹ በሙሉ ይጠፋሉ፤+እሱም ከሕልውና ውጭ ይሆናል።+ 11  አባት የሌላቸው ልጆችህን ተዋቸው፤እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ፤መበለቶችህም በእኔ ይታመናሉ።” 12  ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ ጽዋውን እንዲጠጡ ያልተፈረደባቸውም እንኳ ለመጠጣት የሚገደዱ ከሆነ አንተ እንዴት ከቅጣት ታመልጣለህ? ከቅጣት አታመልጥም፤ ጽዋውን ትጠጣለህና።”+ 13  “በራሴ ምያለሁና” ይላል ይሖዋ፤ “ቦስራ አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤+ ለነቀፋ፣ ለጥፋትና ለእርግማንም ትዳረጋለች፤ ከተሞቿም ሁሉ ለዘለቄታው ባድማ ይሆናሉ።”+ 14  ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ በእሷም ላይ ውጡ፤ለጦርነት ተዘጋጁ።”+ 15  “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር፣በሰዎችም መካከል የተናቅክ አድርጌሃለሁና።+ 16  አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣በጣም ረጅሙን ኮረብታ የያዝክ ሆይ፣የነዛኸው ሽብርናየልብህ እብሪት አታሎሃል። ጎጆህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ላይ ብትሠራም፣እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ። 17  “ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች።+ በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል። 18  ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+ 19  “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ+ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርረዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 20  ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በኤዶም ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና* በቴማን+ ነዋሪዎች ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፦ ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም። ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+ 21  እነሱ ሲወድቁ ከሚሰማው ታላቅ ድምፅ የተነሳ ምድር ተናወጠች። ጩኸት ይሰማል! ድምፁም እስከ ቀይ ባሕር+ ድረስ አስተጋብቷል። 22  እነሆ፣ ልክ እንደ ንስር ወደ ላይ ይወጣና ተወንጭፎ ይወርዳል፤+በቦስራም ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+ በዚያ ቀን የኤዶም ተዋጊዎች ልብ፣ምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።” 23  ስለ ደማስቆ+ የተነገረ መልእክት፦ “ሃማትና+ አርጳድክፉ ወሬ በመስማታቸው አፍረዋል። በፍርሃት ይቀልጣሉ። ባሕሩ ታውኳል፤ ጸጥ ሊል አይችልም። 24  ደማስቆ ወኔ ከዳት። ለመሸሽ ወደ ኋላ ዞረች፤ ይሁንና ብርክ ያዛት። ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትጭንቅና ሥቃይ ያዛት። 25  የምትወደሰው ከተማ፣ በሐሴትም የተሞላችው መዲናእንዴት ሳትተው ቀረች? 26  ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉና፤በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 27  “የደማስቆን ቅጥር በእሳት አነዳለሁ፤እሳቱም የቤንሃዳድን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።”+ 28  ይሖዋ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ስለመታቸው ስለ ቄዳርና+ ስለ ሃጾር መንግሥታት እንዲህ ይላል፦ “ተነሱ፤ ወደ ቄዳር ውጡ፤የምሥራቅንም ሰዎች አጥፉ። 29  ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው፣የድንኳን ሸራዎቻቸውና ዕቃዎቻቸው ሁሉ ይወሰዳሉ። ግመሎቻቸውን ይነጠቃሉ፤‘ሽብር በየቦታው ነግሦአል!’ ብለው ወደ እነሱ ይጮኻሉ።” 30  “እናንተ የሃጾር ነዋሪዎች፣ ሽሹ፤ ወደ ሩቅ ቦታም ተሰደዱ! ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ” ይላል ይሖዋ። “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በእናንተ ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤በእናንተም ላይ አንድ ዕቅድ አቅዷል።” 31  “በሰላም፣ ተረጋግቶ በተቀመጠው ብሔር ላይተነሱ፣ ውጡ!” ይላል ይሖዋ። “በሮችም ሆነ መቀርቀሪያዎች የሉትም፤ ብቻቸውንም ይኖራሉ። 32  ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፤ብዛት ያላቸው ከብቶቻቸውም በምርኮ ይወሰዳሉ። በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን ሰዎች+ነፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ሁሉ* እበትናቸዋለሁ፤ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ። 33  “ሃጾርም የቀበሮዎች ጎሬ፣ለዘለቄታውም ባድማ ትሆናለች። በዚያ ማንም ሰው አይኖርም፤አንድም ሰው በእሷ ውስጥ አይቀመጥም።” 34  በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ኤላምን+ አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ 35  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ የብርታታቸው ምንጭ* የሆነውን የኤላምን+ ቀስት እሰብራለሁ። 36  ከአራቱ የሰማያት ዳርቻዎች፣ አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፤ እኔም እነዚህ ነፋሳት በሚነፍሱበት አቅጣጫ ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተበተኑት ሰዎችም የማይሄዱበት ብሔር አይኖርም።’” 37  “ኤላማውያንን በጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት በሚሹ* ሰዎች ፊት አሸብራለሁ፤ በእነሱም ላይ ጥፋትን ይኸውም የሚነድ ቁጣዬን አመጣለሁ” ይላል ይሖዋ። “ፈጽሞ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍ እሰዳለሁ።” 38  “እኔም ዙፋኔን በኤላም+ አደርጋለሁ፤ ከዚያም ስፍራ ንጉሡንና መኳንንቱን አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ። 39  “በዘመኑ መጨረሻ ግን ከኤላም ተማርከው የተወሰዱትን እሰበስባለሁ” ይላል ይሖዋ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

“የውጊያ ሁካታ ድምፅ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በዙሪያዋም።”
ወይም “የበጎች ጉረኖ።”
ወይም “በረባዳማ ሜዳዎችሽ።”
ወይም “የመከረውን ምክርና።”
ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።
በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
ወይም “በሁሉም አቅጣጫ።”
ቃል በቃል “መነሻ።”
ወይም “ነፍሳቸውን በሚሹ።”