በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ኤርምያስ 3:1-25

የመጽሐፉ ይዘት

  • እስራኤል የፈጸመችው ታላቅ ክህደት (1-5)

  • እስራኤልና ይሁዳ አመነዘሩ (6-11)

  • ስሐ እንዲገቡ የቀረበ ጥሪ (12-25)

3  ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?” ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+ “አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።   “ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ። አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል? በምድረ በዳ እንዳለ ዘላን*አንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው። በዝሙትሽና በክፋትሽምድሪቱን በከልሽ።+   ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤+የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም። አንቺ ዝሙት አዳሪ እንደሆነች ሚስት፣ ዓይን አውጣ ነሽ፤*ኀፍረት የሚባል ነገር አታውቂም።+   አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!+   ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’ አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”+  በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+  ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+  ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+  አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች።+ 10  ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።” 11  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና* ተገኝታለች።+ 12  ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን+ አውጅ፦ “‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’+ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም”*+ ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም። 13  ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች* ጋር አመነዘርሽ፤* ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’” 14  “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ* ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።+ 15  እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤+ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል። 16  በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም። 17  በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤+ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤+ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።” 18  “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ 19  እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’+ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር። 20  ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።” 21  በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ድምፅ ተሰምቷል፤አዎ፣ የእስራኤል ልጆች ለቅሶና ልመና ተሰምቷል፤እነሱ መንገዳቸውን አጣመዋልና፤አምላካቸውን ይሖዋን ረስተዋል።+ 22  “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ። ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+ “እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+ 23  ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው።+ በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።+ 24  ይሁንና አሳፋሪው ነገር* ከልጅነታችን ጀምሮ አባቶቻችን የደከሙበትን ሁሉ፣+መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በልቷል። 25  ኀፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ውርደታችንም ይሸፍነን፤እኛና አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ እስካሁን ድረስበአምላካችን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፤+ የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ዓረብ።”
ቃል በቃል “ዝሙት አዳሪ የሆነች ሚስት ያላት ዓይነት ግንባር አለሽ።”
ወይም “ነፍሷን ጻድቅ አድርጋ።”
ቃል በቃል “ፊቴን አልጥልም።”
ወይም “ከባዕድ አማልክት።”
ቃል በቃል “መንገዶችሽን ለእንግዶች ዘረጋሽ።”
“ባላችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “አጋሯን።”
ወይም “አሳፋሪው አምላክ።”