በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ኢሳይያስ 32:1-20

የመጽሐፉ ይዘት

  • ንጉሥና ገዢዎች ለፍትሕ ይገዛሉ (1-8)

  • ደንታ ቢስ ሴቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (9-14)

  • መንፈስ ሲፈስ የሚገኝ በረከት (15-20)

32  እነሆ፣ ንጉሥ+ ለጽድቅ ይነግሣል፤+መኳንንትም ፍትሕ ለማስፈን ይገዛሉ።   እያንዳንዱም ከነፋስ እንደ መከለያ፣*ከውሽንፍር እንደ መሸሸጊያ፣*ውኃ በሌለበት ምድር እንደ ጅረት፣+በደረቅ ምድርም እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።   በዚያ ጊዜ፣ የሚያዩ ሰዎች ዓይኖች አይጨፈኑም፤የሚሰሙ ሰዎችም ጆሮዎች በትኩረት ያዳምጣሉ።   የችኩሎች ልብ እውቀትን ያሰላስላል፤የሚንተባተብ ምላስም አቀላጥፎና አጥርቶ ይናገራል።+   የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው ከእንግዲህ ለጋስ አይባልም፤ሥርዓት የሌለው ሰውም ትልቅ ሰው አይባልም፤   የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው የማይረባ ነገር ይናገራልና፤ደግሞም በይሖዋ ላይ ክህደት ለመፈጸምና* የውሸት ቃል ለመናገር፣እንዲሁም የተራበ ሰው የሚበላ ነገር እንዳያገኝና*የተጠማ ሰው የሚጠጣ ነገር እንዳያገኝ ለማድረግልቡ ክፋትን ያውጠነጥናል።+   ሥርዓት የሌለው ሰው የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች መጥፎ ናቸው፤+ድሃው ትክክል የሆነውን ነገር በሚናገርበት ጊዜም እንኳየተጎሳቆለውን ሰው በውሸት ቃል ለማጥፋትአሳፋሪ ለሆነ ምግባር ድጋፍ ይሰጣል።+   ለጋስ ሰው ግን ስለ ልግስና ያስባል፤ዘወትር የልግስና* ተግባር ለመፈጸም ይተጋል።   “እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተነሱ፤ ድምፄንም ስሙ! እናንተ ግድየለሽ ሴቶች ልጆች፣+ የምናገረውን ነገር በትኩረት አዳምጡ! 10  እናንተ ግድየለሾች፣ ከአንድ ዓመት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትሸበራላችሁ፤ምክንያቱም የወይን ፍሬ የምትለቅሙበት ጊዜ ሲያልፍ የተሰበሰበ ፍሬ አይኖርም።+ 11  እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተንቀጥቀጡ! እናንተ ግድየለሾች፣ ተሸበሩ! ልብሳችሁን በሙሉ አውልቁ፤በወገባችሁም ላይ ማቅ ታጠቁ።+ 12  ስለ መልካሙ እርሻና ፍሬያማ ስለሆነው ወይንበሐዘን ደረታችሁን ምቱ። 13  የሕዝቤን ምድር እሾህና አሜኬላ ይወርሱታልና፤በደስታ ተሞልተው የነበሩትን ቤቶች ሁሉ፣አዎ፣ በሐሴት ተሞልታ የነበረችውን ከተማ ይሸፍናሉ።+ 14  የማይደፈረው ማማ ባዶ ሆኗልና፤ሁካታ የነበረበት ከተማ ወና ቀርቷል።+ ኦፌልና+ መጠበቂያ ግንቡ ለዘለቄታው ጠፍ ሆነዋል፤የዱር አህዮች መፈንጫናየመንጎች መሰማሪያ ሆነዋል፤+ 15  ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስብን፣+ምድረ በዳውም የፍራፍሬ እርሻ እስከሚሆን፣የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ እስከሚቆጠር ድረስ ነው።+ 16  ከዚያም በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በፍራፍሬ እርሻም ጽድቅ ይኖራል።+ 17  የእውነተኛ ጽድቅ ውጤት ሰላም፣+የእውነተኛ ጽድቅ ፍሬም ዘላቂ ጸጥታና ደህንነት ይሆናል።+ 18  ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ የመኖሪያ ስፍራ፣አስተማማኝ በሆነ መኖሪያና ጸጥታ በሰፈነበት የማረፊያ ቦታ ይኖራል።+ 19  ሆኖም በረዶው ጫካውን ያወድማል፤ከተማዋም ሙሉ በሙሉ ትፈራርሳለች። 20  እናንተ በውኃዎች ሁሉ ዳር ዘር የምትዘሩ፣በሬውንና አህያውንም የምትለቁ* ደስተኞች ናችሁ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “መጠለያ።”
ወይም “እንደ መጠጊያ።”
ወይም “ፈሪሃ አምላክ የጎደለው ድርጊት ለመፈጸምና።”
ወይም “የተራበ ሰው ነፍስ የሚበላ ነገር እንዳታገኝና።”
ወይም “የተቀደሰ።”
ወይም “የምትፈቱ።”