በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

አስቴር 10:1-3

የመጽሐፉ ይዘት

  • አይሁዳውያን ከጥፋት ተረፉ፤ እንዲሁም ተደሰቱ (1-3)

10  ንጉሥ አሐሽዌሮስ በምድሪቱና በባሕር ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎች የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አደረገ።  ንጉሡ ያከናወናቸው ታላላቅና አስደናቂ ሥራዎች በሙሉ እንዲሁም መርዶክዮስን+ ከፍ ከፍ እንዲያደርገው+ ስላነሳሳው ስለ መርዶክዮስ ታላቅነት የሚገልጸው ዘገባ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት+ ዘመን ስለተከናወኑ ነገሮች በሚተርከው መጽሐፍ+ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?  አይሁዳዊው መርዶክዮስ ከንጉሥ አሐሽዌሮስ ቀጥሎ ያለ ሁለተኛ ሰው ነበር። በአይሁዳውያን መካከል ትልቅ ቦታ የነበረው፣* በብዙ ወንድሞቹ ዘንድ የተከበረ፣ ለወገኖቹ ጥቅም የቆመ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ሁሉ ደህንነት የሚቆረቆር* ሰው ነበር።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ከፍ ተደርጎ ይታይ የነበረ።”
ቃል በቃል “ሰላም የሚናገር።”