በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

አሞጽ 9:1-15

የመጽሐፉ ይዘት

  • ከአምላክ ፍርድ ማምለጥ አይቻልም (1-10)

  • የዳዊትን ዳስ መልሼ አቆማለሁ (11-15)

9  ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።+   በመቃብር* ለመደበቅ ወደ ታች ቢቆፍሩምእጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማያት ቢወጡምከዚያ አወርዳቸዋለሁ።   ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁምፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ።+ ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩምበዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ።   ጠላቶቻቸው ማርከው ቢወስዷቸውበዚያ ሰይፍ አዛለሁ፤ ሰይፉም ይገድላቸዋል፤+ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ዓይኔን በእነሱ ላይ አደርጋለሁ።+   ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን* ይነካልና፤እሷም ትቀልጣለች፤+ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤+ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች።+   ‘ደረጃዎቹን በሰማያት የሚሠራው፣ከምድርም በላይ ሕንፃውን* የሚገነባው፣ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+ስሙ ይሖዋ ነው።’+   ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች* አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ። ‘እስራኤልን ከግብፅ ምድር፣+ ፍልስጤማውያንን ከቀርጤስ፣+ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁም?’+   ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+ ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።   ‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋናአንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉየእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ።+ 10  “ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉበሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’ 11  ‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤+በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤*ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤+ 12  በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’+ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ። 13  ‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤+ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+ኮረብቶችም ሁሉ በወይን ይጥለቀለቃሉ።*+ 14  ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+የወይን ተክል ተክለው ወይኑን ይጠጣሉ፤+አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+ 15  ‘በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፤ከሰጠኋቸውም ምድር ላይዳግመኛ አይነቀሉም’+ ይላል አምላክህ ይሖዋ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ምድሪቱን።”
ወይም “ክብ ጣሪያ፤ ባለ ቅስት ጣሪያ።”
ወይም “ለእኔ እንደ ኩሽ ልጆች።”
ወይም “ክፍተቶቻቸውን እጠግናለሁ።”
ቃል በቃል “ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።”