በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

አሞጽ 3:1-15

የመጽሐፉ ይዘት

  • የአምላክን ፍርድ ማወጅ (1-8)

    • ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ሚስጥሩን ይገልጣል (7)

  • ለሰማርያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (9-15)

3  “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይሖዋ ስለ እናንተ ይኸውም ከግብፅ ምድር ስላወጣሁት ስለ መላው ብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦   ‘በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ እኔ የማውቀው እናንተን ብቻ ነው።+ ስለዚህ ለፈጸማችሁት በደል ሁሉ ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ።+   ሁለት ሰዎች ለመገናኘት ሳይስማሙ* አብረው ይጓዛሉ?   አንበሳ አድኖ ሳይዝ በጫካ ውስጥ ያገሳል? ደቦል አንበሳስ ምንም ነገር ሳይዝ በዋሻው ውስጥ ሆኖ ያጉረመርማል?   ወጥመድ ሳይዘጋጅ* ወፍ መሬት ላይ ይጠመዳል? ወጥመድስ ምንም ነገር ሳይዝ ይፈነጠራል?   በከተማ ውስጥ ቀንደ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይሸበርም? በከተማው ውስጥ ጥፋት ቢከሰት ይህን ያደረገው ይሖዋ አይደለም?   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሚስጥሩን* ሳይገልጥምንም ነገር አያደርግምና።+   አንበሳ አገሳ!+ የማይፈራ ማን ነው? ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ተናገረ! ትንቢት የማይናገር ማን ነው?’+   ‘በአሽዶድ በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎችደግሞም በግብፅ ምድር በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች ላይ አውጁት። እንዲህ በሉ፦ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤+በመካከሏ ያለውን ሁከትናበውስጧ የሚፈጸመውን ግፍ ተመልከቱ።+ 10  በማይደፈሩ ማማዎቻቸው ውስጥ ዓመፅንና ጥፋትን የሚያከማቹ ሰዎችትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አያውቁምና” ይላል ይሖዋ።’ 11  ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ጠላት ምድሪቱን ይከባል፤+ብርታትሽን ያሟጥጣል፤የማይደፈሩ ማማዎችሽም ይበዘበዛሉ።’+ 12  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት ቅልጥም ወይም የጆሮ ቁራጭ ነጥቆ እንደሚወስድ ሁሉበሰማርያ ባማረ አልጋና ምርጥ በሆነ ድንክ አልጋ* የሚቀመጡየእስራኤል ሰዎችም ተነጥቀው ይወሰዳሉ።’+ 13  ‘ስሙ፤ የያዕቆብንም ቤት አስጠንቅቁ’* ይላል የሠራዊት አምላክ የሆነው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 14  ‘እስራኤልን ለፈጸመው የዓመፅ ድርጊት* ሁሉ ተጠያቂ በማደርገው ቀን+የቤቴልንም መሠዊያዎች ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+የመሠዊያው ቀንዶች ተቆርጠው ወደ ምድር ይወድቃሉ።+ 15  የክረምቱን ቤትና የበጋውን ቤት አፈርሳለሁ።’ ‘በዝሆን ጥርስ የተሠሩት ቤቶች ይወድማሉ፤+ትላልቅ* ቤቶችም ይደመሰሳሉ’+ ይላል ይሖዋ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በቀጠሮ ሳይገናኙ።”
“ወጥመድ ላይ የሚደረግ ምግብ ሳይኖር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የሰወረውን ጉዳይ።”
ወይም “በደማስቆ ድንክ አልጋ።”
ወይም “በያዕቆብ ቤት ላይ መሥክሩ።”
ወይም “ወንጀል።”
“ብዙ” ማለትም ሊሆን ይችላል።