በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:1-22

የመጽሐፉ ይዘት

  • ኢየሩሳሌም እንደ መበለት ተደርጋ ተገልጻለች

    • ከተማዋ ብቻዋን ቀረች (1)

    • ጽዮን የፈጸመችው ከባድ ኃጢአት (8, 9)

    • ጽዮን በአምላክ ፊት ተቀባይነት አጣች (12-15)

    • ጽዮንን የሚያጽናናት የለም (17)

א [አሌፍ]* 1  በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች!+ ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!+ በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች!+ ב [ቤት]   በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤+ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል። ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም።+ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤+ ጠላት ሆነውባታል። ג [ጊሜል]   ይሁዳ ተጎሳቁላና ለአስከፊ ባርነት ተዳርጋ+ በግዞት ተወስዳለች።+ በብሔራት መካከል ትቀመጣለች፤+ ምንም ማረፊያ ስፍራ አታገኝም። በተጨነቀች ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ ያዟት። ד [ዳሌት]   በዓል ለማክበር የሚመጣ ስለሌለ ወደ ጽዮን የሚወስዱት መንገዶች አዝነዋል።+ በሮቿ ሁሉ ወና ሆነዋል፤+ ካህናቷም ሲቃ ይዟቸዋል። ደናግሏ* አዝነዋል፤ እሷም አስከፊ ሥቃይ ደርሶባታል። ה []   ባላጋራዎቿ አሁን ጌቶቿ* ሆነዋል፤ ጠላቶቿ ጭንቀት የለባቸውም።+ ከበደሏ ብዛት የተነሳ ይሖዋ ሐዘን አምጥቶባታልና።+ ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው ተወስደዋል።+ ו [ዋው]   የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተገፏል።+ መኳንንቷ መሰማሪያ ቦታ እንዳጡ አጋዘኖች ሆነዋል፤በሚያሳድዳቸውም ፊት አቅም አጥተው ይጓዛሉ። ז [ዛየን]   ኢየሩሳሌም በምትጎሳቆልበትና መኖሪያ በምታጣበት ጊዜ፣በጥንት ዘመን የነበሯትን ውድ ነገሮች ሁሉ ታስታውሳለች።+ ሕዝቧ በጠላት እጅ በወደቀበትና የሚረዳት ባልነበረበት ጊዜ+ጠላቶቿ አዩአት፤ በደረሰባትም ውድቀት ሳቁ።*+ ח[ኼት]   ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ፈጽማለች።+ አስጸያፊ ነገር የሆነችው ለዚህ ነው። ያከብሯት የነበሩ ሁሉ አሁን ናቋት፤ እርቃኗን አይተዋልና።+ እሷ ራሷም ትቃትታለች፤+ በኀፍረትም ፊቷን ታዞራለች። ט [ቴት]   ርኩሰቷ ቀሚሷ ላይ አለ። ወደፊት የሚገጥማትን ቆም ብላ አላሰበችም።+ ውድቀቷ አስደንጋጭ ነበር፤ የሚያጽናናትም የለም። ይሖዋ ሆይ፣ ጉስቁልናዬን ተመልከት፤ ጠላት ራሱን ከፍ ከፍ አድርጓልና።+ י [ዮድ] 10  ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል።+ ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራትወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና።+ כ [ካፍ] 11  ነዋሪዎቿ ሁሉ ሲቃ ይዟቸዋል፤ የሚበላ ነገር ይፈልጋሉ።+ ምግብ ለማግኘትና በሕይወት ለመቆየት* ብቻ ሲሉ ያሏቸውን ውድ ነገሮች ሰጥተዋል። ይሖዋ ሆይ፣ እይ ደግሞም ተመልከት፤ እንደማትረባ ሴት ሆኛለሁና።* ל [ላሜድ] 12  በዚህ መንገድ የምታልፉ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ ከምንም የማይቆጠር ነገር ነው? እዩ፤ ደግሞም ተመልከቱ! ይሖዋ በሚነድ ቁጣው ቀን እንድሠቃይ ያደረገበትን፣በእኔ ላይ የደረሰውን ሥቃይ የመሰለ ሥቃይ አለ?+ מ [ሜም] 13  ከከፍታ ቦታ ወደ አጥንቶቼ እሳት ላከ፤+ በእያንዳንዳቸውም ላይ አየለባቸው። ለእግሬ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላ እንድመለስ አስገደደኝ። የተጣለች ሴት አድርጎኛል። ቀኑን ሙሉ ታምሜአለሁ። נ [ኑን] 14  በደሎቼ እንደ ቀንበር ታስረዋል፤ በእጁም ተገምደዋል። አንገቴ ላይ ተደርገዋል፤ ጉልበቴም ተዳክሟል። ይሖዋ መቋቋም ለማልችላቸው ሰዎች አሳልፎ ሰጥቶኛል።+ ס [ሳሜኽ] 15  ይሖዋ በውስጤ ያሉትን ኃያላን በሙሉ አስወገደ።+ ወጣቶቼን ለማድቀቅ በእኔ ላይ ጉባኤ ጠርቷል።+ ይሖዋ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረግጧል።+ ע [አይን] 16  በእነዚህ ነገሮች የተነሳ አለቅሳለሁ፤+ ዓይኖቼ እንባ ያፈሳሉ። ሊያጽናናኝ ወይም መንፈሴን* ሊያድስ የሚችል ሰው ከእኔ ርቋልና። ወንዶች ልጆቼ ተጥለዋል፤ ጠላት አይሏልና። פ [] 17  ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤+ የሚያጽናናትም የለም። በያዕቆብ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ ይሖዋ ትእዛዝ አስተላልፏል።+ ኢየሩሳሌም ለእነሱ አስጸያፊ ነገር ሆናለች።+ צ [ጻዴ] 18  ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ ትእዛዙን ተላልፌአለሁና።*+ እናንተ ሰዎች ሁሉ፣ አዳምጡ፤ ሥቃዬንም ተመልከቱ። ደናግሌና* ወጣት ወንዶቼ በግዞት ተወስደዋል።+ ק [ኮፍ] 19  ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነሱ ግን ከዱኝ።+ ካህናቴና ሽማግሌዎቼ በሕይወት ለመቆየት* ብለውየሚበላ ነገር ሲፈልጉ በከተማዋ ውስጥ አለቁ።+ ר [ረሽ] 20  ይሖዋ ሆይ፣ ተመልከት፤ በከባድ ጭንቀት ተውጫለሁና። አንጀቴም ተላወሰ። ልቤ በውስጤ እጅግ ተረብሿል፤ የለየለት ዓመፀኛ ሆኛለሁና።+ በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤+ በቤት ውስጥ ደግሞ ሞት አለ። ש [ሺን] 21  ሰዎች ሲቃዬን ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለደረሰብኝ ጥፋት ሰምተዋል። ይህን ጥፋት ስላመጣህ ደስ ተሰኝተዋል።+ አንተ ግን የተናገርከውን ቀን በእነሱ ላይ ታመጣለህ፤+ በዚያን ጊዜ እነሱ እንደ እኔ ይሆናሉ።+ ת [ታው] 22  ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ በሠራኋቸው በደሎች ሁሉ የተነሳእኔን እንደቀጣኸኝ፣ እነሱንም ቅጣቸው።+ ለቅሶዬ በዝቷልና፤ ልቤም ታሟል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

የመጀመሪያዎቹ አራት ምዕራፎች በዕብራይስጥ ፊደላት ቅደም ተከተል የተዘጋጁ ሙሾዎች ናቸው።
ወይም “ወጣት ሴቶቿ።”
ቃል በቃል “ራሶቿ።”
ወይም “ፈነደቁ።”
ወይም “ነፍስን ለመመለስ።”
ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው።
ወይም “ነፍሴን።”
ቃል በቃል “በአፉ ላይ ዓመፅ ፈጽሜአለሁ።”
ወይም “ወጣት ሴቶቼና።”
ወይም “ነፍስን ለመመለስ።”