በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ምሳሌ 19:1-29

የመጽሐፉ ይዘት

  • ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ቶሎ አይቆጣም (11)

  • ‘ጨቅጫቃ ሚስት እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት’ (13)

  • ‘ልባም ሚስት የምትገኘው ከይሖዋ ነው’ (14)

  • “ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ” (18)

  • ምክርን መስማት ጥበብ ነው (20)

19  ሞኝ ከመሆንና ውሸት ከመናገርድሃ ሆኖ ንጹሕ አቋምን* ጠብቆ መመላለስ ይሻላል።+   እውቀት የሌለው ሰው* ጥሩ አይደለም፤+ችኩል* ሰውም ኃጢአት ይሠራል።   የሰውን መንገድ የሚያጣምምበት የገዛ ሞኝነቱ ነው፤ልቡም በይሖዋ ላይ ይቆጣል።   ሀብት ብዙ ወዳጆችን ይስባል፤ድሃን ግን ጓደኛው እንኳ ይተወዋል።+   ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤+ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ከቅጣት አያመልጥም።+   ብዙዎች በተከበረ ሰው* ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ይጥራሉ፤ስጦታ ከሚሰጥ ሰው ጋር ደግሞ ሁሉም ይወዳጃል።   ድሃን ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤+ጓደኞቹማ ምን ያህል ይርቁት!+ እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም።   ማስተዋል* የሚያገኝ ሰው ሁሉ ራሱን* ይወዳል።+ ጥልቅ ግንዛቤን እንደ ውድ ሀብት አድርጎ የሚመለከት ሁሉ ይሳካለታል።*+   ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ይጠፋል።+ 10  ሞኝ ሰው ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤አገልጋይ መኳንንትን ቢገዛማ ምንኛ የከፋ ነው!+ 11  ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል፤+በደልንም መተዉ* ውበት ያጎናጽፈዋል።+ 12  የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ* ግሳት ነው፤+ሞገሱ ግን በሣር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው። 13  ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ መከራ ያመጣል፤+ጨቅጫቃ ሚስትም * ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+ 14  ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው።+ 15  ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ታካች ሰውም ይራባል።*+ 16  ትእዛዝን የሚጠብቅ ሕይወቱን* ይጠብቃል፤+መንገዱን ቸል የሚል ይሞታል።+ 17  ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ 18  ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ፤+ለእሱም ሞት ተጠያቂ አትሁን።*+ 19  ግልፍተኛ ሰው ይቀጣል፤ልታድነው ብትሞክር እንኳ በተደጋጋሚ እንዲህ ለማድረግ ትገደዳለህ።+ 20  የኋላ ኋላ ጥበበኛ እንድትሆንምክርን ስማ፤ ተግሣጽንም ተቀበል።+ 21  ሰው በልቡ ብዙ ነገር ያቅዳል፤የሚፈጸመው ግን የይሖዋ ፈቃድ* ነው።+ 22  የሰው ተወዳጅ ባሕርይ ታማኝ ፍቅሩ ነው፤+ውሸታም ከመሆን ድሃ መሆን ይሻላል። 23  ይሖዋን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤+እንዲህ የሚያደርግ ሰው ጥሩ እረፍት ያገኛል፤ ጉዳትም አይደርስበትም።+ 24  ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ሆኖም ወደ አፉ እንኳ መመለስ ይሳነዋል።+ 25  ተሞክሮ የሌለው ብልህ+ እንዲሆን ፌዘኛን ምታው፤+ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኝም አስተዋይ የሆነን ሰው ውቀሰው።+ 26  አባቱን የሚበድልና እናቱን የሚያባርር ልጅኀፍረትና ውርደት ያመጣል።+ 27  ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን መስማት ከተውክእውቀት ከሚገኝበት ቃል ትርቃለህ። 28  የማይረባ ምሥክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤+የክፉዎችም አፍ ክፋትን ይሰለቅጣል።+ 29  ፌዘኞች ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤+ለሞኞች ጀርባ ደግሞ ዱላ ተዘጋጅቷል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “በእግሩ የሚጣደፍ።”
ወይም “ለጋስ በሆነ ሰው።”
ቃል በቃል “ልብ።”
ወይም “ነፍሱን።”
ቃል በቃል “መልካም ነገር ያገኛል።”
ቃል በቃል “በደልንም ማለፉ።”
ወይም “ደቦል አንበሳ።”
ወይም “ነዝናዛ ሚስትም።”
ወይም “ታካች ነፍስም ትራባለች።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ወሮታ።”
ወይም “የእሱንም ሞት አትመኝ።” ቃል በቃል “ለእሱ ሞት ነፍስህን አታንሳ።”
ወይም “ዓላማ።”