በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ምሳሌ 1:1-33

የመጽሐፉ ይዘት

  • የምሳሌዎቹ ዓላማ (1-7)

  • መጥፎ ጓደኝነት የሚያስከትለው መዘዝ (8-19)

  • እውነተኛ ጥበብ በአደባባይ ትጮኻለች (20-33)

1  የእስራኤል ንጉሥ፣+ የዳዊት ልጅ+ የሰለሞን ምሳሌዎች፦+   ጥበብንና+ ተግሣጽን ለመማር፣*ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣   ጥልቅ ማስተዋል፣ ጽድቅ፣+ ጥሩ ፍርድና*+ቅንነት* የሚያስገኝ ተግሣጽ ለመቀበል፣+   ተሞክሮ ለሌላቸው ብልሃትን፣+ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት።+   ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤+ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤+   ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልንእንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።+   ይሖዋን መፍራት* የእውቀት መጀመሪያ ነው።+ ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+   ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤+የእናትህንም መመሪያ* አትተው።+   ለራስህ የሚያምር የአበባ ጉንጉን፣+ለአንገትህም ውብ ጌጥ ይሆንልሃል።+ 10  ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።+ 11  እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ። ደም ለማፍሰስ እናድባ። ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን። 12  እንደ መቃብር፣* በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን። 13  ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን። 14  ከእኛ ጋር ልትተባበር ይገባል፤*ሁላችንም የሰረቅነውን እኩል እንካፈላለን።”* 15  ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው። እግርህን ከመንገዳቸው አርቅ፤+ 16  እግሮቻቸው ክፉ ነገር ለመሥራት ይሮጣሉና፤ደም ለማፍሰስ ይጣደፋሉ።+ 17  ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው። 18  እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤የሰዎችን ሕይወት* ለማጥፋት ያደፍጣሉ። 19  በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት የሚሹ መንገዳቸው ይህ ነው፤እንዲህ ያለው ትርፍ የተጠቃሚዎቹን ሕይወት* ያጠፋል።+ 20  እውነተኛ ጥበብ+ በጎዳና ላይ ትጮኻለች።+ በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።+ 21  ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን* ላይ ሆና ትጣራለች። በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦+ 22  “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ? እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ? እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?+ 23  ለወቀሳዬ ምላሽ ስጡ።*+ እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።+ 24  በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤+ 25  ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤ 26  እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤+ 27  የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ። 28  በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤+ 29  ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤+ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።+ 30  ምክሬን አልተቀበሉም፤ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል። 31  ስለዚህ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላሉ፤*+በገዛ ራሳቸውም ምክር* ከልክ በላይ ይጠግባሉ። 32  ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል። 33  እኔን የሚሰማ ሰው ግን ተረጋግቶ ይኖራል፤+መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ለማወቅ።”
ወይም “ፍትሕና።”
ወይም “ሚዛናዊነት።”
ወይም “በጥልቅ ማክበር።”
ወይም “ሕግ፤ ትምህርት።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል።”
ወይም “አንድ የጋራ ከረጢት (ቦርሳ) ይኖረናል።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “ራስ።”
ወይም “ስወቅሳችሁ ተመለሱ።”
ቃል በቃል “የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ።”
ወይም “ውጥን፤ ዕቅድ።”