በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

መዝሙር 8:1-9

የመጽሐፉ ይዘት

  • የአምላክ ክብርና የሰው ክብር

    • ‘ስምህ ምንኛ የከበረ ነው!’ (1, 9)

    • “ሟች ሰው ምንድን ነው?” (4)

    • ‘የግርማ ዘውድ ደፋህለት’ (5)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የዳዊት ማህሌት። 8  ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው፤ግርማህ ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ እንዲል አድርገሃል!*+   ከባላጋራዎችህ የተነሳ፣ከልጆችና ከሕፃናት አፍ በሚወጡ ቃላት+ ብርታትህን አሳየህ፤ይህም ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ነው።   የጣቶችህን ሥራ ሰማያትን፣አንተ የሠራሃቸውን ጨረቃንና ከዋክብትን ስመለከት፣+   ታስበው ዘንድ ሟች ሰው ምንድን ነው?ትንከባከበውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+   ከመላእክት* በጥቂቱ አሳነስከው፤የክብርና የግርማ ዘውድም ደፋህለት።   በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሥልጣን ሰጠኸው፤+ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አደረግክለት፦   መንጎቹንና ከብቶቹን ሁሉ፣እንዲሁም የዱር አራዊትን፣+   የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ ከእግሩ በታች አደረግክለት።   ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው!

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ግርማህ ከሰማያት በላይ የተነገረ!” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “እንደ አምላክ ካሉት።”