በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

መኃልየ መኃልይ 4:1-16

የመጽሐፉ ይዘት

  • እረኛው (1-5)

    • ‘ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ ውብ ነሽ’ (1)

  • ልጃገረዷ (6)

  • እረኛው (7-16ሀ)

    • “ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል” (9)

  • ልጃገረዷ (16ለ)

4  “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው። ፀጉርሽ ከጊልያድ+ ተራሮችእየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።   ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውናታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም።   ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤ንግግርሽም አስደሳች ነው። በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።   አንገትሽ+ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች+ ሁሉ የተንጠለጠሉበትንናበንብርብር ድንጋዮች የተገነባውንየዳዊት ማማ+ ይመስላል።   ሁለቱ ጡቶችሽበአበቦች መካከል የተሰማሩ፣መንታ የሆኑ ሁለት የሜዳ ፍየል ግልገሎችን ይመስላሉ።”+   “የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትወደ ከርቤው ተራራናወደ ነጭ ዕጣኑ ኮረብታ እሄዳለሁ።”+   “ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤+እንከንም የለብሽም።   ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤አዎ፣ ከሊባኖስ+ አብረን እንሂድ። ከአማና አናት፣ከሰኒር ጫፍ፣ ከሄርሞን+ አናት፣ከአንበሳ ዋሻዎች፣ ከነብር ተራሮች ውረጂ።   እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል፤+በአንድ አፍታ እይታሽ፣ከሐብልሽ ዶቃዎች በአንዱ ልቤን ማርከሽዋል። 10  እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ!+ የፍቅር መግለጫሽ ከወይን ጠጅ፣የሽቶሽም መዓዛ ከየትኛውም ዓይነት ቅመም+ እጅግ ይበልጣል!+ 11  ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ።+ ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤+የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው። 12  እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት። 13  ቡቃያሽ* ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎችደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት* ነው፤ 14  በተጨማሪም ናርዶስ፣+ ሳፍሮን፣* ጠጅ ሣር፣+ ቀረፋ፣+ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትና*+ሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች+ ያሉበት ገነት ነው። 15  አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድናከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ።+ 16  የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና። በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ።* መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።” “ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባናምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
“ገላሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የአትክልት ስፍራ።”
የአበባ ዓይነት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሽቶ ለመሥራት የሚያገለግል ጥሩ መዓዛ ያለው ንጥረ ነገር የሚገኝበትን ዛፍ ያመለክታል።
ወይም “በቀስታ ንፈስ።”