በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

መሳፍንት 3:1-31

የመጽሐፉ ይዘት

  • ይሖዋ እስራኤላውያንን ፈተናቸው (1-6)

  • ኦትኒኤል፣ የመጀመሪያው መስፍን (7-11)

  • መስፍኑ ኤሁድ ወፍራም የሆነውን ንጉሥ ኤግሎንን ገደለው (12-30)

  • መስፍኑ ሻምጋር (31)

3  ይሖዋ ከከነአን ጋር በተደረገው ጦርነት ያልተካፈሉትን እስራኤላውያን ሁሉ እንዲፈትኗቸው+ ሲል በምድሪቱ ላይ እንዲኖሩ የፈቀደላቸው ብሔራት እነዚህ ናቸው  (ይህን ያደረገው ከዚህ በፊት ተዋግተው የማያውቁት በኋላ ላይ የመጡት የእስራኤላውያን ትውልዶች የውጊያ ልምድ እንዲያገኙ ነው)፦  አምስቱ የፍልስጤም+ ገዢዎች፣ ከነአናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያን+ እንዲሁም ከበዓልሄርሞን ተራራ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት* + ድረስ በሚዘልቀው የሊባኖስ+ ተራራ የሚኖሩት ሂዋውያን።+  እነዚህ ብሔራት እስራኤላውያን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ለአባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዛት ይጠብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ የእስራኤላውያን መፈተኛ ሆነው አገልግለዋል።+  በመሆኑም እስራኤላውያን በከነአናውያን፣ በሂታውያን፣ በአሞራውያን፣ በፈሪዛውያን፣ በሂዋውያን እና በኢያቡሳውያን መካከል ይኖሩ ነበር።+  እነሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ያገቡ፣ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነሱ ወንዶች ልጆች ይድሩ የነበረ ሲሆን የእነሱን አማልክትም ማገልገል ጀመሩ።+  ስለዚህ እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን ይሖዋንም ረሱ፤ ባአልንና+ የማምለኪያ ግንዶችን* + አገለገሉ።  በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ለሜሶጶጣሚያው* ንጉሥ ለኩሻንሪሻታይምም አሳልፎ ሸጣቸው። እስራኤላውያን ኩሻንሪሻታይምን ለስምንት ዓመት አገለገሉት።  ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10  የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። 11  ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች።* ከዚያም የቀናዝ ልጅ ኦትኒኤል ሞተ። 12  እስራኤላውያንም እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር ማድረግ ጀመሩ።+ ስለዚህ ይሖዋ የሞዓብ+ ንጉሥ ኤግሎን በእስራኤላውያን ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አድርገው ነበር። 13  በተጨማሪም አሞናውያንንና+ አማሌቃውያንን+ በእነሱ ላይ አመጣባቸው። እነሱም በእስራኤላውያን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የዘንባባ ዛፎች ከተማን+ ያዙ። 14  እስራኤላውያንም የሞዓብን ንጉሥ ኤግሎንን 18 ዓመት አገለገሉ።+ 15  ከዚያም እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ ጮኹ፤+ ይሖዋም ግራኝ+ የሆነውን ቢንያማዊውን+ የጌራን ልጅ ኤሁድን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው።+ ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በእሱ በኩል ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን ግብር ላኩ። 16  በዚህ ጊዜ ኤሁድ ርዝመቱ አንድ ክንድ* የሆነ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ሠርቶ ከልብሱ ሥር በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። 17  ከዚያም ግብሩን ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን አቀረበ። ኤግሎን በጣም ወፍራም ነበር። 18  ኤሁድ ግብሩን ሰጥቶ እንደጨረሰ ግብሩን ተሸክመው የመጡትን ሰዎች አሰናበታቸው። 19  እሱ ግን በጊልጋል+ የሚገኙት የተቀረጹ ምስሎች* ጋ ሲደርስ ተመልሶ በመሄድ “ንጉሥ ሆይ፣ በሚስጥር የምነግርህ አንድ መልእክት አለኝ” አለ። ንጉሡም “እስቲ አንዴ ጸጥታ!” አለ። በዚህ ጊዜ አገልጋዮቹ ሁሉ ጥለውት ወጡ። 20  ንጉሡ፣ ሰገነት ላይ በሚገኘው ቀዝቀዝ ያለ የግል ክፍሉ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ወደ እሱ ቀረበ። ከዚያም ኤሁድ “ከአምላክ ዘንድ ለአንተ የመጣ መልእክት አለኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከዙፋኑ* ተነሳ። 21  ስለዚህ ኤሁድ ግራ እጁን ሰዶ በቀኝ ጭኑ በኩል የነበረውን ሰይፍ በመምዘዝ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠው። 22  ከስለቱ በኋላም እጀታው ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ኤሁድ ሰይፉን ከሆዱ መልሶ ስላላወጣው ስለቱ በስብ ተሸፈነ፤ ፈርሱም ተዘረገፈ። 23  ኤሁድም በበረንዳው* በኩል ወጣ፤ ሰገነት ላይ ያለውን ክፍል በሮች ግን ዘግቶ ቆልፏቸው ነበር። 24  እሱም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጥተው ሲያዩ ሰገነት ላይ ያለው ክፍል በሮች ተቆልፈው ነበር። በመሆኑም “ቀዝቀዝ ባለው ውስጠኛ ክፍል እየተጸዳዳ* ይሆናል” አሉ። 25  እነሱም እስኪያፍሩ ድረስ ጠበቁ፤ ሆኖም ሰገነት ላይ የሚገኘውን ክፍል በሮች እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ ቁልፉን ወስደው በሮቹን ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ ወለል ላይ ተዘርሮ ተመለከቱ! 26  ኤሁድ ግን እነሱ ቆመው ሲጠባበቁ ሳለ አመለጠ፤ በተቀረጹት ምስሎች* + በኩል አድርጎም በሰላም ወደ ሰኢራ ደረሰ። 27  እዚያም እንደደረሰ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ቀንደ መለከት ነፋ፤+ እስራኤላውያንም ከተራራማው አካባቢ ወጥተው በእሱ መሪነት አብረውት ወረዱ። 28  ከዚያም “ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” አላቸው። እነሱም ተከትለውት በመሄድ ሞዓባውያን እንዳይሻገሩ የዮርዳኖስን መልካዎች* ያዙባቸው፤ አንድም ሰው እንዲሻገር አልፈቀዱም። 29  በዚያን ጊዜም ጠንካራና ጀግና የሆኑ 10,000 ሞዓባውያንን ገደሉ፤+ አንድም ሰው አላመለጠም።+ 30  በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል እጅ ተንበረከከ፤ ምድሪቱም ለ80 ዓመት አረፈች።* + 31  ከእሱ በኋላ፣ 600 ፍልስጤማውያንን+ በከብት መውጊያ+ የገደለው የአናት ልጅ ሻምጋር+ ተነሳ፤ እሱም እስራኤልን አዳነ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃማት መግቢያ።”
ቃል በቃል “ለአራምናሃራይም።”
ቃል በቃል “የአራምን።”
ወይም “ሰላም አገኘች።”
ወደ 38 ሴንቲ ሜትር ገደማ ርዝመት ያለውን አጭር ክንድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
“የድንጋይ ካባዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ከተቀመጠበት።”
“በአየር ማስገቢያው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “እግሩን እየሸፈነ።”
“በድንጋይ ካባዎቹ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወንዝ ማቋረጥ የሚቻልበት ጥልቀት የሌለው የወንዝ ክፍል።
ወይም “ሰላም አገኘች።”