በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ሆሴዕ 6:1-11

የመጽሐፉ ይዘት

  • ወደ ይሖዋ እንዲመለሱ የቀረበ ጥሪ (1-3)

  • ሕዝቡ ታማኝ ፍቅር ማሳየቱን አልቀጠለም (4-6)

    • ታማኝ ፍቅር ከመሥዋዕት ይበልጣል (6)

  • የሕዝቡ ምግባር አሳፋሪ ነው (7-11)

6  “ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤እሱ ቦጫጭቆናል፤+ ሆኖም ይፈውሰናል። እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል።   ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል። በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤እኛም በፊቱ እንኖራለን።   ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን። የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብወደ እኛ ይመጣል።”   “ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና።   ከዚህም የተነሳ በነቢያቴ አማካኝነት እቆራርጣቸዋለሁ፤+በአፌም ቃል እገድላቸዋለሁ።+ በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።+   ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣*ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና።+   እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ።+ በዚያም እኔን ከዱኝ።   ጊልያድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ናት፤+ከተማዋ በደም ጨቅይታለች።+   የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው። በሴኬም+ መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና። 10  በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ። በዚያ ኤፍሬም ያመነዝራል፤+እስራኤል ራሱን አርክሷል።+ 11  በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜመከር ይጠብቅሃል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ምሕረት።”