በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ሆሴዕ 13:1-16

የመጽሐፉ ይዘት

  • ጣዖት አምላኪ የሆነው ኤፍሬም ይሖዋን ረሳ (1-16)

    • “ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?” (14)

13  “ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤል ነገዶች መካከል ትልቅ ቦታ ነበረው።+ ሆኖም ባአልን በማምለክ በደል በመፈጸሙ+ ሞተ።   አሁንም ተጨማሪ ኃጢአት ይሠራሉ፤በብራቸውም ለራሳቸው የብረት ምስሎች* ይሠራሉ፤+በጥበብ ጣዖቶችን ያበጃሉ፤ ሁሉም የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራቸው ናቸው። ‘መሥዋዕት የሚያቀርቡት ሰዎች ጥጃዎቹን ይሳሙ’+ በማለት ለእነሱ ይናገራሉ።   ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ይሆናሉ፤አውሎ ነፋስ ከአውድማ ላይ ጠራርጎ እንደሚወስደው እብቅ፣በጭስ ማውጫም በኩል እንደሚወጣ ጭስ ይሆናሉ።   ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ፤+ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም ነበር፤ከእኔም ሌላ አዳኝ የለም።+   እኔ በምድረ በዳ፣ ድርቅ ባለበትም ምድር ተንከባከብኩህ።+   በግጦሽ መሬታቸው ላይ ከበሉ በኋላ ጠገቡ፤+በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ። ከዚህም የተነሳ ረሱኝ።+   ስለዚህ እንደ አንበሳ፣+በመንገድም ዳር እንደሚያደባ ነብር እሆንባቸዋለሁ።   ግልገሎቿን እንደተነጠቀች ድብ ሆኜ እመጣባቸዋለሁ፤ደረታቸውንም እዘነጥላለሁ። በዚያ እንደ አንበሳ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አውሬ ይቦጫጭቃቸዋል።   እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ላይ ስለተነሳህ፣ረዳትህንም ስለተቃወምክ ያጠፋሃል። 10  ‘ንጉሥና መኳንንት ስጠኝ’ ብለህ ነበር፤ታዲያ በከተሞችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ+ንጉሥህ የት አለ? ገዢዎችህስ* የት አሉ?+ 11  እኔም ተቆጥቼ ንጉሥ ሰጠሁህ፤+በታላቅ ቁጣዬም አስወግደዋለሁ።+ 12  የኤፍሬም በደል ታሽጎ ተቀምጧል፤*ኃጢአቱም ተከማችቷል። 13  ምጥ እንደያዛት ሴት ይሆናል። እሱ ግን ጥበበኛ ልጅ አይደለም፤የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ በቦታው ላይ አይገኝም። 14  ከመቃብር* እጅ እዋጃቸዋለሁ፤ከሞትም እታደጋቸዋለሁ።+ ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?+ መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ?+ ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል። 15  በቄጠማዎች መካከል ተመችቶት ቢያድግ እንኳየምሥራቅ ነፋስ ይኸውም የይሖዋ ነፋስ ይመጣል፤የውኃ ጉድጓዱ እንዲደርቅ፣ ምንጩም እንዲነጥፍ ለማድረግ ከበረሃ ይመጣል። ውድ የሆኑ ንብረቶቹ ሁሉ የሚገኙበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።+ 16  ሰማርያ በአምላኳ ላይ ስላመፀች+ ተጠያቂ ትሆናለች።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ልጆቻቸው ይፈጠፈጣሉ፤የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ቀልጠው የተሠሩ ሐውልቶች።”
ቃል በቃል “ፈራጆችህስ።”
ወይም “ተጠብቋል።”
ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።