በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ–አዲስ ዓለም ትርጉም

ሆሴዕ 12:1-14

የመጽሐፉ ይዘት

  • ኤፍሬም ወደ ይሖዋ መመለስ ይኖርበታል (1-14)

    • ያዕቆብ ከአምላክ ጋር ታገለ (3)

    • ያዕቆብ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት አልቅሶ ለመነ (4)

12  “ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል። ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል። ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤+ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ።+   ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤+ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ድርጊቱም ብድራት ይከፍለዋል።+   በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤+ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ።+   ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ። ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።”+ አምላክ በቤቴል አገኘው፤ በዚያም እኛን አነጋገረን፤+   እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።+የመታሰቢያ ስሙ* ይሖዋ ነው።+   “ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤+ታማኝ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤+ምንጊዜም በአምላክህ ተስፋ አድርግ።   ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤እሱ ማጭበርበር ይወዳል።+   ኤፍሬም ‘በእርግጥ እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤+ሀብት አካብቻለሁ።+ ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል።   ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+ በተወሰነው ጊዜ* እንደነበረው ሁሉ፣እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ። 10  ለነቢያቱ ተናገርኩ፤+ራእዮቻቸውን አበዛሁ፤በነቢያቱም በኩል ምሳሌዎችን ተናገርኩ። 11  በጊልያድ ማታለልና* ውሸት አለ።+ በጊልጋል በሬዎችን ሠውተዋል፤+በተጨማሪም መሠዊያዎቻቸው በእርሻ ትልም ላይ እንዳለ የድንጋይ ክምር ናቸው።+ 12  ያዕቆብ ወደ አራም* ምድር ሸሸ፤+እስራኤል+ ሚስት ለማግኘት ሲል በዚያ አገለገለ፤+ሚስት ለማግኘትም ሲል በግ ጠባቂ ሆነ።+ 13  ይሖዋ በነቢይ አማካኝነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣው፤+በነቢይም አማካኝነት ጠበቀው።+ 14  ኤፍሬም ግን እጅግ በደለው፤+ደም በማፍሰስ የፈጸመው በደል በላዩ ላይ ይሆናል፤ላመጣበትም ነቀፋ ጌታው ብድራት ይከፍለዋል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የሚታወስበት ስም።”
“በበዓል ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ምትሃትና፤ አስማትና።”
ወይም “ሶርያ።”