በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

3 ዮሐንስ 1:1-14

 ከሽማግሌው፣ ከልብ ለምወደው ለተወዳጁ ጋይዮስ።  የተወደድክ ወንድም፣ ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ሁሉ፣ በሁሉም ነገር እንዲሳካልህና ጥሩ ጤንነት እንዲኖርህ እጸልያለሁ።  ምክንያቱም ወንድሞች መጥተው እውነትን አጥብቀህ እንደያዝክ ሲመሠክሩ በመስማቴ እጅግ ደስ ብሎኛል፤ አሁንም በእውነት ውስጥ እየተመላለስክ ያለህ መሆኑ በጣም አስደስቶኛል።  ልጆቼ አሁንም በእውነት ውስጥ እየተመላለሱ እንዳሉ ከመስማት የበለጠ አመስጋኝ እንድሆን የሚያደርገኝ ምንም ነገር የለም።  የተወደድክ ወንድም፣ ለወንድሞች፣ ያውም ለማታውቃቸው ወንድሞች በምታደርገው ነገር ሁሉ የታመነ ሥራ እያከናወንክ ነው፤  እነሱም በጉባኤው ፊት ስለ አንተ ፍቅር መሥክረዋል። እባክህ፣ በሚጓዙበት ጊዜ አምላክ ደስ በሚሰኝበት ሁኔታ ሸኛቸው።  ምክንያቱም ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ የወጡት ለስሙ ሲሉ ነው።  ስለዚህ በእውነት ውስጥ አብረን የምንሠራ እንሆን ዘንድ እንዲህ ያሉትን ሰዎች በእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ የማስተናገድ ግዴታ አለብን።  ለጉባኤው የጻፍኩት ነገር ነበር፤ ሆኖም በመካከላቸው የመሪነት ቦታ መያዝ የሚፈልገው ዲዮጥራጢስ ከእኛ በአክብሮት የሚቀበለው ምንም ነገር የለም። 10  ከመጣሁ ስለ እኛ ክፉ ቃላት በመለፍለፍ የሚሠራው ሥራ ሁሉ አንድ በአንድ እንዲነሳ የማደርገው በዚህ ምክንያት ነው። ይህም አልበቃ ብሎት እሱ ራሱ ወንድሞችን በአክብሮት አይቀበልም፤ እነሱን ለመቀበል የሚፈልጉትንም ለመከልከልና ከጉባኤ ለማባረር ይጥራል። 11  የተወደድክ ወንድም፣ መጥፎ የሆነውን ነገር ሳይሆን ጥሩ የሆነውን ነገር ኮርጅ። መልካም የሚያደርግ የአምላክ ወገን ነው። መጥፎ የሚያደርግ አምላክን አላየውም። 12  ድሜጥሮስ በሁሉም ወንድሞች ተመሥክሮለታል፤ እውነት ራሱም ይህን አረጋግጧል። እንዲያውም እኛም ጭምር እየመሠከርን ነው፤ የምንሰጠው ምሥክርነት ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃለህ። 13  ብዙ የምጽፍልህ ነገር ነበረኝ፤ ሆኖም ከዚህ በላይ በቀለምና በብዕር ልጽፍልህ አልፈልግም። 14  ከዚህ ይልቅ በአካል እንደማይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንነጋገራለን። ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ሰላምታዬን ለወዳጆች በየስማቸው አቅርብልኝ።

የግርጌ ማስታወሻዎች