በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

2 ዮሐንስ 1:1-13

 ከሽማግሌው፣ ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆቿ:- ከልብ እወዳችኋለሁ፣ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን ያወቁ ሁሉ ይወዷችኋል፤  የምንወዳችሁ በውስጣችን በሚኖረው እውነት የተነሳ ነው፤ ይህም እውነት አብሮን ለዘላለም ይኖራል።  አባት ከሆነው አምላክና የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ከእውነትና ከፍቅር ጋር ከእኛ ጋር ይሆናል።  ከልጆችሽ መካከል አንዳንዶቹ ከአብ በተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት እየተመላለሱ መሆናቸውን ስላወቅኩ እጅግ ደስ ብሎኛል።  ስለሆነም እመቤት ሆይ፣ የምጽፍልሽ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ነው፤ ይህም አዲስ ትእዛዝ ሳይሆን ከመጀመሪያ ጀምሮ የተቀበልነው ነው።  ፍቅር ማለት ደግሞ በትእዛዛቱ መሠረት መመላለሳችንን እንቀጥል ዘንድ ነው። እናንተ ከመጀመሪያ እንደሰማችሁት ትእዛዙ በፍቅር መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው።  ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መምጣቱን አምነው የማይቀበሉ ብዙ አሳሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። እንዲህ ያለ ሰው አሳሳችና ፀረ ክርስቶስ ነው።  ሙሉ ሽልማት እንድታገኙ እንጂ የደከምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።  አልፎ የሚሄድና በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖር ሁሉ አምላክ የለውም። አብና ወልድ ያሉት በዚህ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ነው። 10  ማንም ሰው ወደ እናንተ ቢመጣና ይህን ትምህርት ባያመጣ ፈጽሞ በቤታችሁ አትቀበሉት ወይም ሰላም አትበሉት። 11  ምክንያቱም ሰላም የሚለው ሰው የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናል። 12  የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ቢኖረኝም በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት እንደማነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። 13  የተመረጠችው እህትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።

የግርጌ ማስታወሻዎች