በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

2 ቆሮንቶስ 5:1-21

5  ምድራዊ ቤታችን የሆነው ይህ ድንኳን ቢፈርስ በእጅ የተሠራ ቤት ሳይሆን በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ ሕንጻ ከአምላክ እንደምናገኝ እናውቃለን።  ከሰማይ የምናገኘውን ለመልበስ እየናፈቅን በዚህ መኖሪያ ቤት እንቃትታለን፤  ይህን በእርግጥ ከለበስን ራቁታችንን ሆነን አንገኝም።  እንዲያውም በዚህ ድንኳን ውስጥ ያለነው ከብዶን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ሟች የሆነው በሕይወት እንዲዋጥ ይኼኛውን ማውለቅ ሳይሆን ያኛውን መልበስ እንፈልጋለን።  ለዚህ ነገር ያዘጋጀን አምላክ ነው፤ ለሚመጣው ነገር መያዣ ይኸውም መንፈሱን የሰጠንም እሱ ነው።  ስለዚህ ምንጊዜም ልበ ሙሉ ነን፤ በተጨማሪም መኖሪያችን በሆነው አካል እስካለን ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን እናውቃለን፤  የምንመላለሰው በእምነት እንጂ በማየት አይደለምና።  ሆኖም ልበ ሙሉ ነን፤ ደግሞም ከዚህ አካል ርቀን መኖሪያችንን ከጌታ ጋር ብናደርግ ደስ ይለናል።  በተጨማሪም መኖሪያችንን ከእሱ ጋር ብናደርግም ሆነ ከእሱ ርቀን ብንኖር ዓላማችን እሱን ደስ ማሰኘት ነው። 10  ምክንያቱም እያንዳንዱ በአካሉ ላደረገው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር፣ እንደሠራው ሥራ ብድራት እንዲቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ቀርበን ማንነታችን ይገለጥ ዘንድ ይገባል። 11  እንግዲህ ጌታን መፍራት እንደሚገባን ስለምናውቅ ሰዎች የምንናገረውን እንዲቀበሉ ለማሳመን ምንጊዜም እንጥራለን፤ ሆኖም የእኛ ማንነት በአምላክ ፊት የተገለጠ ነው። ይሁንና ሕሊናችሁ የእኛን ማንነት እንድትገነዘቡ እንደረዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። 12  እኛ ራሳችንን እንደ አዲስ ብቁ አድርገን ማቅረባችን አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በልብ ሳይሆን በውጫዊ መልክ ለሚኩራሩ መልስ መስጠት ትችሉ ዘንድ በእኛ እንድትኮሩ እያነሳሳናችሁ ነው። 13  አእምሯችንን ብንስት ለአምላክ ብለን ነው፤ ጤናማ አእምሮ ቢኖረን ደግሞ ለእናንተ ብለን ነው። 14  አንድ ሰው ለሁሉም መሞቱን ስለተረዳን ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ሁሉም ቀድሞውኑ ሞተዋል፤ 15  በሕይወት ያሉት ከእንግዲህ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለእነሱ ለሞተውና ለተነሳው እንዲኖሩ እሱ ለሁሉም ሞቷል። 16  ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም ሰው በሥጋዊ ሁኔታ አንመለከትም። ክርስቶስን በሥጋዊ ሁኔታ እናውቀው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በዚህ መልክ አናውቀውም። 17  በመሆኑም ማንም ከክርስቶስ ጋር አንድ ከሆነ አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፤ እነሆ፣ አዳዲስ ነገሮች ወደ ሕልውና መጥተዋል! 18  ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት በክርስቶስ አማካኝነት ከራሱ ጋር ካስታረቀንና የማስታረቅ አገልግሎት ከሰጠን አምላክ ነው፤ 19  ይኸውም አምላክ በክርስቶስ አማካኝነት ዓለምን ከራሱ ጋር ከማስታረቁም በላይ በደላቸውን አልቆጠረባቸውም፤ ለእኛ ደግሞ የእርቁን ቃል ሰጥቶናል። 20  እኛ ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ አምባሳደሮች ነን፤ ይህም አምላክ በእኛ አማካኝነት እየተማጸነ ያለ ያክል ነው። ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን “ከአምላክ ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን። 21  እኛ በእሱ አማካኝነት በአምላክ ፊት ጻድቅ እንድንሆን ኃጢአት የማያውቀው እሱ ለእኛ የኃጢአት መሥዋዕት ተደረገ።

የግርጌ ማስታወሻዎች