በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

2 ቆሮንቶስ 3:1-18

3  እኛ ራሳችንን እንደ አዲስ ብቁ አድርገን ማቅረባችን ነው? ወይስ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለእናንተ ወይም ከእናንተ የብቃት ማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን?  ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን ላይ የተጻፈ ደብዳቤያችን እናንተ ራሳችሁ ናችሁ።  ምክንያቱም እናንተ አገልጋዮች በሆንነው በእኛ አማካኝነት በቀለም ሳይሆን በሕያው አምላክ መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላቶች ላይ ሳይሆን በሥጋ ጽላቶች ይኸውም በልብ ላይ የተጻፋችሁ የክርስቶስ ደብዳቤ እንደሆናችሁ በግልጽ ታይቷል።  በመሆኑም በክርስቶስ በኩል በአምላክ ላይ እንዲህ ያለ እምነት አለን።  ብቃታችንን ራሳችን በራሳችን ያገኘነው እንደሆነ አድርገን አናስብም፤ ከዚህ ይልቅ ብቃታችንን ያገኘነው ከአምላክ ነው፤  እሱም የአዲስ ቃል ኪዳን አገልጋዮች ይኸውም የተጻፈ ሕግ ሳይሆን የመንፈስ አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አድርጎናል፤ ምክንያቱም የተጻፈው ሕግ ለሞት ፍርድ ይዳርጋል፤ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል።  በተጨማሪም የእስራኤል ልጆች ከፊቱ ክብር የተነሳ የሙሴን ፊት ትኩር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ የሞት ፍርድ የሚያስከትለውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው ሕግ በክብር ይኸውም በሚጠፋ ክብር ከመጣ  የመንፈስ አገልግሎት እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም?  ኩነኔ የሚያስከትለው የሕግ አገልግሎት ክብራማ ከሆነ ጽድቅ የሚያስገኘው አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የላቀ ክብር አይኖረውም! 10  እንዲያውም ከዚህ አንጻር ሲታይ በአንድ ወቅት ክብራማ ሆኖ የነበረው፣ ከእሱ የላቀ ክብር ያለው በመምጣቱ ምክንያት ክብሩ ተገፏል። 11  የሚጠፋው በክብር ከመጣ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም! 12  ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ተስፋ ስላለን ታላቅ የመናገር ነፃነት አለን፤ 13  ደግሞም የእስራኤል ልጆች የዚያን የሚሻረውን መጨረሻ በትኩረት እንዳይመለከቱ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን በነበረበት ጊዜ እንደነበረው አናደርግም። 14  ሆኖም እነሱ አእምሯቸው ደንዝዟል። አሮጌው ቃል ኪዳን በተነበበ ቁጥር ያው መሸፈኛ እስከ ዛሬ ድረስ እንደጋረዳቸው ነው፤ ምክንያቱም መሸፈኛው የሚወገደው በክርስቶስ አማካኝነት ነው። 15  እንዲያውም እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቁጥር ልባቸው በመሸፈኛ እንደተሸፈነ ነው። 16  ሆኖም አንድ ሰው ወደ ይሖዋ ዞር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል። 17  ይሖዋ መንፈስ ነው፤ የይሖዋ መንፈስ ባለበት ደግሞ ነፃነት አለ። 18  እኛ ሁላችንም ባልተሸፈነ ፊት የይሖዋን ክብር እንደ መስተዋት ስናንጸባርቅ ያንኑ መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ ይህም የሚሆነው መንፈስ የሆነው ይሖዋ በሚያከናውንበት በዚያው መንገድ ነው።

የግርጌ ማስታወሻዎች