በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

1 ጴጥሮስ 5:1-14

5  ስለዚህ እኔም ከእነሱ ጋር ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምሥክር እንዲሁም ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ ስለሆንኩ በመካከላችሁ ላሉት ሽማግሌዎች ይህን ጥብቅ ምክር እሰጣለሁ:-  በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክ መንጋ ጠብቁ፤ በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን ለማገልገል በመጓጓት፣  የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ።  የእረኞች አለቃ እንዲገለጥ በሚደረግበት ጊዜ የማይጠፋ የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።  በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ። ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፤ ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።  ስለዚህ በተገቢው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤  የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።  የማስተዋል ስሜቶቻችሁን ጠብቁ፤ ንቁዎች ሆናችሁ ኑሩ። ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል።  ሆኖም በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ ተገንዝባችሁ በእምነት ጸንታችሁ በመቆም ተቃወሙት። 10  ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ አንድነት አማካኝነት ወደ ዘላለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ ግን እሱ ራሱ ሥልጠናችሁን ይፈጽማል፣ ጽኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል እንዲሁም ጠንካሮች ያደርጋችኋል። 11  ለዘላለም ኃይል ለእሱ ይሁን። አሜን። 12  እኔ ታማኝ ወንድም አድርጌ በምቆጥረው በስልዋኖስ* አማካኝነት ይህን በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍኩላችሁም ማበረታቻ ለመስጠትና ይህ የአምላክ እውነተኛ ጸጋ እንደሆነ ከልብ ለመመሥከር ነው፤ በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ። 13  እንደ እናንተ የተመረጠችው በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ ልጄ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። 14  በፍቅር እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላችሁ ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

1ጴጥ 5:12 * ወይም፣ “ሲላስ።”