በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

1 ተሰሎንቄ 2:1-20

2  ወንድሞች፣ የእኛ ወደ እናንተ መምጣት ፍሬ ቢስ ሆኖ እንዳልቀረ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁ ምንም ጥርጥር የለውም፤  ይሁንና በመጀመሪያ (እናንተም እንደምታውቁት) በፊልጵስዩስ መከራ ከተቀበልንና እንግልት ከደረሰብን በኋላ የአምላክን ምሥራች በከፍተኛ ትግል ለእናንተ ለመናገር በአምላካችን እርዳታ እንደምንም ብለን እንዴት ድፍረት እንዳገኘን ታውቃላችሁ።  የምንሰጠው ምክር ከተሳሳተ ሐሳብ ወይም ከመጥፎ ዓላማ የመነጨ ወይም ደግሞ ማታለያ ያዘለ አይደለም፤  ሆኖም ምሥራቹን በአደራ ለመቀበል ብቁ እንደሆንን አምላክ ያረጋገጠልን እንደመሆናችን መጠን የምንናገረው ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን አምላክ ለማስደሰት ብለን ነው።  እንዲያውም (እንደምታውቁት) ወደ እናንተ ስንመጣ የሽንገላ ቃል የተናገርንበት ወይም ጎምጅተን ያን ለመሸፈን ሰበብ ያቀረብንበት ጊዜ የለም፤ ለዚህም አምላክ ምሥክር ነው!  በተጨማሪም የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን መጠን እናንተን ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም ልንሆንባችሁ እንችል የነበረ ቢሆንም እንኳ ከሰዎች ይኸውም ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ክብር ለማግኘት አልፈለግንም።  ከዚህ ይልቅ የምታጠባ እናት ልጆቿን እንደምትንከባከብ እኛም በመካከላችሁ በነበርንበት ጊዜ በገርነት ተንከባከብናችሁ።  በመሆኑም ለእናንተ ጥልቅ ፍቅር ስላለን የአምላክን ምሥራች ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ጭምር ለእናንተ ለማካፈል ዝግጁዎች ነበርን፤ ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ እጅግ የተወደዳችሁ ነበራችሁ።  ወንድሞች፣ ድካማችንንና ልፋታችንን እንደምታስታውሱ ጥርጥር የለውም። የአምላክን ምሥራች የሰበክንላችሁ፣ ማናችሁንም ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም እንዳንሆንባችሁ ብለን ሌት ተቀን እየሠራን ነው። 10  አማኞች በሆናችሁት በእናንተ መካከል እንዴት ታማኞች፣ ጻድቃንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን እንደተገኘን እናንተ ምሥክሮች ናችሁ፤ አምላክም ምሥክር ነው። 11  ከዚህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ አባት ለልጆቹ እንደሚያደርገው እያንዳንዳችሁን እንዴት እንመክራችሁ፣ እናጽናናችሁና አጥብቀን እናሳስባችሁ እንደነበረ በሚገባ ታውቃላችሁ፤ 12  ይህንም ያደረግነው ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ በጠራችሁ አምላክ ፊት በአግባቡ መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው። 13  አምላክን ያለማቋረጥ የምናመሰግነውም ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ከእኛ የሰማችሁትን የአምላክ ቃል በተቀበላችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን አማኞች በሆናችሁት በእናንተ ላይ በእርግጥ እየሠራ እንዳለ እንደ አምላክ ቃል አድርጋችሁ ተቀብላችሁታል፤ ደግሞም የአምላክ ቃል ነው። 14  ወንድሞች፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸውን በይሁዳ የሚገኙ የአምላክ ጉባኤዎች ምሳሌ ኮርጃችኋል፤ ምክንያቱም እነሱ በአይሁዳውያን እጅ መከራ እየተቀበሉ እንዳሉ ሁሉ እናንተም በገዛ አገራችሁ ሰዎች እጅ ተመሳሳይ መከራ መቀበል ጀምራችኋል፤ 15  አይሁዳውያን ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ሳይቀር የገደሉ ከመሆኑም በላይ በእኛ ላይ ስደት አድርሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ አምላክን እያስደሰቱ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰውን ሁሉ ጥቅም የሚጻረሩ ናቸው፤ 16  አሕዛብ ይድኑ ዘንድ ለእነሱ እንዳንሰብክ እንቅፋት ሊፈጥሩብን ይሞክራሉ፤ እንዲህ በማድረግም ሁልጊዜ ኃጢአታቸው እንዲሞላ ያደርጋሉ። ይሁንና ቁጣው የሚገለጽበት ጊዜ ደርሷል። 17  በእኛ በኩል ግን ወንድሞች፣ በልብ ሳይሆን በአካል ከእናንተ ለአጭር ጊዜ ለመለየት በተገደድንበት ወቅት ለእናንተ ካለን ታላቅ ናፍቆት የተነሳ ፊታችሁን ለማየት ብርቱ ጥረት አደረግን። 18  ከዚህ የተነሳ ወደ እናንተ መምጣት ፈልገን ነበር፤ አዎ፣ እኔ ጳውሎስ ከአንዴም ሁለቴ ሞክሬ ነበር፤ ሆኖም ሰይጣን መንገድ ዘጋብን። 19  ጌታችን ኢየሱስ በሚገኝበት* ጊዜ በእሱ ፊት ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የሐሴታችን አክሊል ምንድን ነው? በእርግጥ እናንተ አይደላችሁም? 20  በእርግጥም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

1ተሰ 2:19 * ከተጨማሪው መረጃ ላይ 5ኛውን ርዕስ ተመልከት።