በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

የሐዋርያት ሥራ 6:1-15

6  በዚያን ወቅት የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማከፋፈል ሥራ መበለቶቻቸው ቸል ስለተባሉባቸው ዕብራይስጥ ተናጋሪ በሆኑት አይሁዳውያን ላይ ማጉረምረም ጀመሩ።  ስለዚህ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን በሙሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው:- “በማዕድ ምግብ ለማከፋፈል ስንል የአምላክን ቃል የማስተማር ሥራችንን ብንተው ተገቢ አይሆንም።  ስለዚህ ወንድሞች፣ ለዚህ አስፈላጊ ሥራ እንድንሾማቸው ከእናንተ መካከል በመልካም ምግባራቸው የተመሠከረላቸው በመንፈስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ወንዶች ምረጡ፤  እኛ ግን በጸሎትና ቃሉን በማስተማሩ ሥራ ላይ ሙሉ በሙሉ እናተኩራለን።”  ይህ የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኘ፤ ስለሆነም በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት የተለወጠውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ፤  ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።  ከዚህም የተነሳ የአምላክ ቃል እያደገ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄደ፤ በጣም ብዙ ካህናትም ይህን እምነት ተቀበሉ።  እስጢፋኖስም ጸጋና ኃይል ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ይፈጽም ነበር።  ይሁን እንጂ ነፃ የወጡ ሰዎች ምኩራብ ተብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት የሆኑ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁም ከቀሬና፣ ከእስክንድርያ፣ ከኪልቅያና ከእስያ ሰዎች አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ተከራከሩት፤ 10  ይሁንና ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። 11  ስለዚህ “ይህ ሰው በሙሴና በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” የሚሉ ሰዎች በስውር አዘጋጁ። 12  በተጨማሪም ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን እንዲሁም ጸሐፍትን አነሳሱ፤ ከዚያም በድንገት መጡና አስገድደው ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ ወሰዱት። 13  የሐሰት ምሥክሮችም አቀረቡ፤ እነሱም እንዲህ አሉ:- “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን የሚቃወም ነገር ከመናገር ሊቆጠብ አልቻለም። 14  ለምሳሌ ያህል ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያፈርሰውና ሙሴ ያስተላለፈልንን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” 15  በሳንሄድሪን ሸንጎ ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ ትኩር ብለው ሲያዩት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው።

የግርጌ ማስታወሻዎች