በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ዕብራውያን 5:1-14

5  ምክንያቱም ከሰዎች መካከል የተመረጠ እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት ለኃጢአት መባና መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ የአምላክ በሆኑት ነገሮች ላይ ሰዎችን በመወከል ይሾማል።  እሱ ራሱ ድክመት ስላለበት አላዋቂ የሆኑትንና የሚሳሳቱትን በርኅራኄ ሊይዛቸው ይችላል፤  በዚህም የተነሳ ለሕዝቡ የሚያቀርበውን ያህል ለራሱም የኃጢአት መሥዋዕት ለማቅረብ ይገደዳል።  በተጨማሪም አንድ ሰው ይህን የክብር ቦታ የሚያገኘው እንደ አሮን፣ አምላክ ሲጠራው ብቻ ነው እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም።  ክርስቶስም ሊቀ ካህናት በመሆን ራሱን አላከበረም፤ ከዚህ ይልቅ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ አባት ሆንኩህ” ብሎ ስለ እሱ የተናገረው፣ ክብር አጎናጸፈው።  ሌላ ቦታ ላይም “በመልከጼዴቅ ሥርዓት መሠረት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ እንደተናገረው ነው።  ክርስቶስ በሥጋ በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ለቅሶና እንባ ምልጃና ልመና አቀረበ፤ አምላካዊ ፍርሃት በማሳየቱም ተሰሚነት አገኘ።  ልጅ ቢሆንም እንኳ ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተማረ፤  ፍጹም ከተደረገም በኋላ የሚታዘዙት ሁሉ ዘላለማዊ መዳን እንዲያገኙ ኃላፊነት ተሰጠው፤ 10  ምክንያቱም በመልከጼዴቅ ሥርዓት መሠረት አምላክ ሊቀ ካህናት ብሎ ጠርቶታል። 11  እሱን በተመለከተ ብዙ የምንናገረው ነገር አለን፤ ይሁንና ጆሯችሁ ስለደነዘዘ ለማስረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው። 12  እንደ እውነቱ ከሆነ ከጊዜው አንጻር አስተማሪዎች ልትሆኑ ይገባችሁ የነበረ ቢሆንም የአምላክን ቅዱስ መልእክት መሠረታዊ ነገሮች እንደገና ከመጀመሪያ ጀምሮ የሚያስተምራችሁ ሰው ትፈልጋላችሁ፤ ደግሞም ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት እንደሚፈልግ ሰው ሆናችኋል። 13  ምክንያቱም ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለሆነ ከጽድቅ ቃል ጋር ትውውቅ የለውም። 14  ጠንካራ ምግብ ግን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት ላሠለጠኑ ጎልማሳ ሰዎች ነው።

የግርጌ ማስታወሻዎች