በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

ዕብራውያን 2:1-18

2  ከእምነት ጎዳና ቀስ በቀስ እየራቅን እንዳንሄድ ለሰማናቸው ነገሮች ከወትሮው የተለየ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።  ምክንያቱም በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ይህን ቃል መተላለፍና አለመታዘዝ ሁሉ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ  ለመጀመሪያ ጊዜ በጌታችን አማካኝነት የተነገረውንና እሱን የሰሙት ሰዎች ለእኛ ያረጋገጡልንን እንዲህ ያለ ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?  አምላክም በምልክቶች እንዲሁም በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል።  እየተናገርንለት ያለውን መጪውን ዓለም ያስገዛው ለመላእክት አይደለም።  ነገር ግን አንድ ምሥክር፣ የሆነ ቦታ ላይ እንዲህ በማለት ማስረጃ አቅርቧል:- “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ወይስ ትንከባከበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?  ከመላእክት ጥቂት አሳነስከው፤ የክብርንና የሞገስን ዘውድ ደፋህለት፤ እንዲሁም በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሾምከው።  ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት።” አምላክ ሁሉንም ነገር ስላስገዛለት ሳያስገዛለት የተወው ምንም ነገር የለም። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም፤  ነገር ግን ከመላእክት ጥቂት ዝቅ እንዲል ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለእያንዳንዱ ሰው ሲል ሞትን ቀምሷል። 10  ሁሉ ነገር የሚኖረው ለአምላክ ነው፤ የሚኖረውም በእሱ አማካኝነት ነው፤ ስለዚህ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ ለመዳን የሚያበቃቸውን ዋና ወኪል በመከራ አማካኝነት ፍጹም ማድረጉ ለእሱ የተገባ ነበር። 11  የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸው፤ ከዚህም የተነሳ እነሱን “ወንድሞች” ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤ 12  ምክንያቱም “ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤ በጉባኤ መካከልም በመዝሙር አወድስሃለሁ” ይላል። 13  ደግሞም “እኔ እምነቴን በእሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል። እንደገናም “እነሆ! እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች” ይላል። 14  ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤ ይኸውም ሞት የማስከተል ኃይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤ 15  እንዲሁም ሞትን በመፍራት በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ለባርነት የተዳረጉትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው። 16  እሱ እየረዳ ያለው መላእክትን እንዳልሆነ የታወቀ ነው፤ ከዚህ ይልቅ እየረዳ ያለው የአብርሃምን ዘር ነው። 17  ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ የግድ እንደ ወንድሞቹ መሆን አስፈለገው። 18  በተፈተነበት ጊዜ እሱ ራሱ መከራ ስለደረሰበት በመፈተን ላይ ላሉት ሊደርስላቸው ይችላልና።

የግርጌ ማስታወሻዎች