በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

ቲቶ 2:1-15

2  አንተ ግን ምንጊዜም ለጤናማ ትምህርት ተስማሚ የሆኑ ነገሮችን ተናገር።  አረጋውያን ወንዶች በልማዶቻቸው ረገድ ልከኞች፣ ቁም ነገረኞች፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው እንዲሁም በእምነት፣ በፍቅርና በጽናት ጤናማዎች ይሁኑ።  በተመሳሳይም አረጋውያን ሴቶች ለቅዱሳን ሰዎች የሚገባ ባሕርይ ያላቸው፣ ስም የማያጠፉ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ እንዲሁም ጥሩ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤  ይህም ወጣት ሴቶችን ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ በመርዳት ባሎቻቸውን የሚወዱ፣ ልጆቻቸውን የሚወዱ፣  ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ንጹሖች፣ በቤት ውስጥ የሚሠሩ፣ ጥሩዎችና ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላቸዋል፤ ይህም የአምላክ ቃል እንዳይሰደብ ያደርጋል።  በተመሳሳይም ወጣት ወንዶች ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው መምከርህን ቀጥል፤  መልካም ሥራ በመሥራት በሁሉም ነገር ራስህን ምሳሌ አድርገህ አቅርብ፣ ንጹሕ የሆነውን አስተምር፣ ቁም ነገረኛ መሆንህን አሳይ፣  ሊነቀፍ የማይችል ጤናማ ንግግር ይኑርህ፤ ይኸውም በተቃዋሚ ወገን ያለ ሰው ስለ እኛ የሚናገረው መጥፎ ነገር አጥቶ እንዲያፍር ነው።  ባሪያዎች በሁሉም ነገር ለጌቶቻቸው ይገዙ፤ እንዲሁም ደስ ያሰኟቸው፤ የአጸፋ ቃል አይመልሱላቸው፤ 10  በተጨማሪም አይስረቁ፣ ከዚህ ይልቅ አዳኛችን የሆነውን አምላክ ትምህርት በሁሉም ነገር ያስውቡ ዘንድ ፍጹም ታማኝነት ያሳዩ። 11  ምክንያቱም ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መዳን የሚያስገኘው ጸጋ ተገልጧል፤ 12  ይህም ጸጋ አምላካዊ ያልሆነ ምግባርንና ዓለማዊ ምኞቶችን ክደን አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና ለአምላክ በማደር እንድንኖር ያስተምረናል፤ 13  በዚህ ሁኔታ አስደሳች የሆነውን ተስፋና የታላቁን አምላክ እንዲሁም የአዳኛችንን የክርስቶስ ኢየሱስን ክብራማ መገለጥ እንጠባበቃለን፤ 14  ክርስቶስ እኛን ከማንኛውም ዓይነት ዓመፅ ለማዳንና ለመልካም ሥራ የሚቀና የእሱ ብቻ የሆነ ሕዝብ ለራሱ ለማንጻት ራሱን ለእኛ ሰጥቷል። 15  በተሰጠህ ሙሉ የማዘዝ ሥልጣን መሠረት እነዚህን ነገሮች በተመለከተ መናገርህን፣ አጥብቀህ መምከርህንና መገሠጽህን ቀጥል። ማንም ሰው ፈጽሞ አይናቅህ።

የግርጌ ማስታወሻዎች