በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት | መጽሐፍ ቅዱስ--አዲስ ዓለም ትርጉም በ2013 ተሻሽሎ የወጣውን ተመልከት

ራእይ 15:1-8

15  እኔም ሌላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ነበሩ። የአምላክ ቁጣ የሚደመደመው በእነዚህ ስለሆነ እነዚህ መቅሰፍቶች የመጨረሻዎቹ ናቸው።  እኔም ከእሳት ጋር የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቁጥር ድል የነሱት የአምላክን በገናዎች ይዘው በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ቆመው አየሁ።  እነሱም የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር:- “ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው። የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በእርግጥ የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ታማኝ ነህ! የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ አምልኮ ያቀርባሉ።”  ከዚህ በኋላም አየሁ፤ የምሥክሩ ድንኳን ቅዱስ ስፍራ በሰማይ ተከፍቶ ነበር፤  ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም ንጹሕና የሚያንጸባርቅ በፍታ ለብሰው እንዲሁም ደረታቸውን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ከቅዱሱ ስፍራ ወጡ።  ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትም አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉ ሰባት የወርቅ ሳህኖችን ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።  ቅዱሱ ስፍራም ከአምላክ ክብርና ከኃይሉ የተነሳ በጭስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሰፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስም ማንም ወደ ቅዱሱ ስፍራ መግባት አልቻለም።

የግርጌ ማስታወሻዎች