ምያንማር

ክፍል ማቅረብ

የስምሪት ስብሰባ መምራት

መንግሥት አዳራሹን መንከባከብ

በጉባኤ ውስጥ በኃላፊነት የሚያገለግሉ ክርስቲያን ወንዶች በሁለት እንደሚከፈሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ እነሱም ‘ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች’ ናቸው። (ፊልጵስዩስ 1:1) አብዛኛውን ጊዜ በእያንዳንዱ ጉባኤ ውስጥ እነዚህን ኃላፊነቶች የሚወጡ በርካታ ወንድሞች ይኖራሉ። ታዲያ የጉባኤ አገልጋዮች እኛን የሚጠቅሙ ምን ሥራዎችን ያከናውናሉ?

የሽማግሌዎች አካልን ያግዛሉ። በየትኛውም ዕድሜ ላይ የሚገኙ የጉባኤ አገልጋዮች መንፈሳዊ አመለካከት ያላቸው፣ እምነት የሚጣልባቸውና በትጋት የሚሠሩ ወንድሞች ናቸው። ከድርጅታዊ አሠራር ጋር የተያያዙ እንዲሁም የመንግሥት አዳራሹን የሚመለከቱ ተደጋጋሚ ሆኖም አስፈላጊ ሥራዎችን ያከናውናሉ። የጉባኤ አገልጋዮች እነዚህን ሥራዎች በማከናወናቸው ሽማግሌዎች በማስተማርና በእረኝነት ሥራዎች ላይ ማተኮር ይችላሉ።

ጠቃሚ የሆነ አገልግሎት ይሰጣሉ። አንዳንድ የጉባኤ አገልጋዮች፣ ወደ ስብሰባ ለሚመጡ ሁሉ ጥሩ አቀባበል እንዲያደርጉ አስተናጋጅ ሆነው ይመደባሉ። ሌሎች ደግሞ በድምፅ ወይም በጽሑፍ ክፍል ውስጥ ያገለግላሉ፤ የሒሳብ አገልጋይ ሆነው ይሠራሉ፤ አሊያም የጉባኤው አባላት የሚሰብኩባቸውን ክልሎች ያከፋፍላሉ። በተጨማሪም የመንግሥት አዳራሹ በአግባቡ እንዲያዝ በማድረግ ረገድ እርዳታ ያበረክታሉ። ከዚህም ሌላ የጉባኤ አገልጋዮች፣ አረጋውያንን እንዲረዱ ሽማግሌዎች ሊጠይቋቸው ይችላሉ። የጉባኤ አገልጋዮች ምንም ዓይነት ኃላፊነት ቢሰጣቸው ሥራቸውን በፈቃደኝነት ስለሚያከናውኑ ሁሉም የጉባኤው አባላት ሊያከብሯቸው ይገባል።—1 ጢሞቴዎስ 3:13

ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ ክርስቲያን ወንዶች ናቸው። ክርስቲያን ወንዶች፣ የጉባኤ አገልጋዮች እንዲሆኑ የሚሾሙት ጥሩ መንፈሳዊ ባሕርያት ስላሏቸው ነው። የጉባኤ አገልጋዮች በስብሰባዎች ላይ ክፍል በማቅረብ እምነታችንን ያጠናክሩልናል። በስብከቱ ሥራ በግንባር ቀደምትነት በመካፈል በቅንዓት እንድናገለግል ያነሳሱናል። ከሽማግሌዎች ጋር ተባብረው በመሥራት በጉባኤው ውስጥ ደስታና አንድነት እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። (ኤፌሶን 4:16) ውሎ አድሮ ደግሞ እነሱም ሽማግሌ ሆነው ለማገልገል የሚያስፈልገውን ብቃት ሊያሟሉ ይችላሉ።

  • የጉባኤ አገልጋዮች ሆነው የሚሾሙት ምን ዓይነት ወንዶች ናቸው?

  • አገልጋዮች የጉባኤው እንቅስቃሴ የተቀላጠፈ እንዲሆን የሚረዱት እንዴት ነው?