በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

አንተስ የይሖዋን ፈቃድ ታደርጋለህ?

አንተስ የይሖዋን ፈቃድ ታደርጋለህ?

የይሖዋ ምሥክሮች ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ፣ እንቅስቃሴያቸው ምን እንደሚመስልና ድርጅታቸው ምን እንደሚያከናውን ለማወቅ ስትል ጊዜ ወስደህ ይህን ብሮሹር በማንበብህ እናመሰግንሃለን። ይህ ብሮሹር በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆኑ ለማወቅ እንዳስቻለህ ተስፋ እናደርጋለን። ስለ አምላክ መማርህን እንድትቀጥል፣ ስለተማርከው ነገር ለቤተሰብህና ለጓደኞችህ እንድትናገር እንዲሁም በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ ከእኛ ጋር እንድትሰበሰብ እናበረታታሃለን።—ዕብራውያን 10:23-25

ስለ ይሖዋ ይበልጥ በተማርክ መጠን ምን ያህል ከልቡ እንደሚወድህ ይበልጥ ማስተዋል ትችላለህ። ይህም አንተም በምላሹ ለእሱ ያለህን ፍቅር ለማሳየት የምትችለውን ሁሉ እንድታደርግ ያነሳሳሃል። (1 ዮሐንስ 4:8-10, 19) ታዲያ አምላክን እንደምትወድ በዕለት ተዕለት ሕይወትህ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው? የአምላክን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መታዘዝ የሚጠቅምህ እንዴት ነው? አንተም ከእኛ ጋር ሆነህ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ምን ሊረዳህ ይችላል? የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪህ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ በደስታ ይነግርሃል፤ ይህ እውቀት አንተም ሆንክ ቤተሰብህ “ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ” በመኖር “የዘላለም ሕይወት” ማግኘት እንድትችሉ ይረዳችኋል።—ይሁዳ 21

በእውነት ጎዳና ላይ እድገት ማድረግህን መቀጠል ትችል ዘንድ ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ እንድታጠና ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን።