በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’

ይህ መጽሐፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርቶች በሕይወትህ ተግባራዊ በማድረግ ከአምላክ ፍቅር ሳትወጣ እንድትኖር ይረዳሃል።

የበላይ አካሉ መልእክት

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል፣ ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ ከአባቱ ፍቅር ሳይወጣ የኖረውን የኢየሱስን ምሳሌ እንዲኮርጁ ግብዣ ያቀርባል።

ምዕራፍ 1

“አምላክን መውደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ በአጭሩ ይናገራል።

ምዕራፍ 2

ጥሩ ሕሊና ይዘህ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?

ሕሊናችን የሚነግረን ነገር ለእኛ ጥሩ ቢመስለንም በአምላክ ዘንድ ትክክል ላይሆን የሚችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 3

አምላክ የሚወዳቸውን ውደድ

ይሖዋ ወዳጆቹ የሚሆኑትን ሰዎች በጥንቃቄ ይመርጣል፤ እኛስ?

ምዕራፍ 4

ለሥልጣን አክብሮት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው?

ቅዱሳን መጻሕፍት፣ በየትኞቹ ሦስት አቅጣጫዎች ለሥልጣን አክብሮት ማሳየት እንደምንችል ይጠቁሙናል።

ምዕራፍ 5

ከዓለም የተለየን ሆነን መኖር የምንችለው እንዴት ነው?

የአምላክ ቃል፣ በየትኞቹ አምስት አቅጣጫዎች ከዓለም መለየት እንደሚኖርብን ይናገራል።

ምዕራፍ 6

ጤናማ መዝናኛ መምረጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምርጫ ለማድረግ የሚረዱ ሦስት ጥያቄዎች ምንድን ናቸው?

ምዕራፍ 7

ልክ እንደ አምላክ ለሕይወት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለህ?

ለሕይወት ዋጋ እንደምንሰጥ ማሳየት የምንችለው የሰውን ሕይወት ባለማጥፋት ብቻ ነው?

ምዕራፍ 8

አምላክ ንጹሕ የሆኑ ሰዎችን ይወዳል

መጽሐፍ ቅዱስ፣ በአምላክ ዓይን ርኩስ እንድትሆን ከሚያደርጉ ልማዶች እንድትርቅ ይረዳሃል።

ምዕራፍ 9

“ከዝሙት ሽሹ”

በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የፆታ ብልግና ይፈጽማሉ። በዚህ ወጥመድ እንዳትወድቅ ምን ይረዳሃል?

ምዕራፍ

ጋብቻ—አፍቃሪ ከሆነው አምላክ የተገኘ ስጦታ

የሰመረ ትዳር እንዲኖርህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ባለትዳር ከሆንክ ደግሞ ትዳርህን ዘላቂ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 11

‘ጋብቻ ክቡር ይሁን’

ትዳርን የሰመረ ለማድረግ የሚረዱ ስድስት ነጥቦች እነሆ!

ምዕራፍ 12

‘ሌሎችን የሚያንጽ መልካም ቃል’ ተናገር

ንግግራችን ሌሎችን ሊጎዳ ወይም ሊያንጽ ይችላል። የመናገር ችሎታህን ይሖዋ በሚፈልገው መንገድ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 13

አምላክ የማይደሰትባቸው በዓሎች

ለአምላክ ክብር ተብለው የሚደረጉ አንዳንድ በዓላት አምላክን ያሳዝኑታል።

ምዕራፍ 14

በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን

ለሌሎች ሐቀኛ ከመሆንህ በፊት ማድረግ ያለብህ ነገር አለ።

ምዕራፍ 15

ከሥራህ እርካታን ማግኘት ትችላለህ

አንድን ሥራ ከመቀበልህ በፊት ልታስብባቸው የሚገቡ አምስት ጥያቄዎች።

ምዕራፍ 16

ዲያብሎስንና መሠሪ ዘዴዎቹን ተቃወም

ሰይጣን ከፍተኛ ኃይል እንዳለው እናውቃለን፤ ሆኖም ይህ ሊያስጨንቀን አይገባም። ለምን?

ምዕራፍ 17

‘እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ገንቡ’

በአምላክ ላይ ያለህን እምነት ለማጠናከርና ከፍቅሩ ሳትወጣ ለመኖር የሚረዱ ሦስት ነገሮች።

ተጨማሪ መረጃ

ከአንድ የተወገደ ግለሰብ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን ይገባል?

ከተወገደ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣችን ተገቢ ነው?

ተጨማሪ መረጃ

ክርስቲያን ሴቶች ራሳቸውን መሸፈን የሚኖርባቸው መቼ ነው? ለምንስ?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከዚህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ልናስብባቸው የሚገቡ ሦስት ነገሮችን ይገልጻል።

ተጨማሪ መረጃ

ለባንዲራ ሰላምታ መስጠት፣ ድምፅ መስጠትና የሲቪል አገልግሎት

ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ንጹሕ ሕሊና እንዲኖርህ የሚረዱ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?

ተጨማሪ መረጃ

ንዑሳን የደም ክፍልፋዮችና የቀዶ ሕክምና ሂደቶች

ከሕክምና ጋር በተያያዘ ሊያጋጥሙህ የሚችሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለመወጣት የሚረዱ ቀላል እርምጃዎች።

ተጨማሪ መረጃ

የማስተርቤሽንን ልማድ ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው?

ይህን መጥፎ ልማድ ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ መረጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍቺና ስለ መለያየት ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ከሆነ ፍቺ የፈጸመ አንድ ሰው ድጋሚ ለማግባት ነፃነት የሚኖረው መቼ ነው?

ተጨማሪ መረጃ

ገንዘብ ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን መፍታት

አንድ ክርስቲያን የእምነት ባልንጀራውን በፍርድ ቤት ሊከሰው ይችላል?