በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!

በስተ ግራ፦ የብሩክሊን ቤቴል ቤተሰብ የገና በዓልን ለመጨረሻ ጊዜ ሲያከብር፣ 1926፤ በስተ ቀኝ፦ የይሖዋ ምሥክሮች የተለዩ መሆናቸውን ሰዎች ያስተውላሉ

 ክፍል 3

የመንግሥቱ መሥፈርቶች—የአምላክን ጽድቅ መፈለግ

የመንግሥቱ መሥፈርቶች—የአምላክን ጽድቅ መፈለግ

 ጎረቤትህን መንገድ ላይ ስታየው ሰላምታ ሰጠኸው። ይህ ጎረቤትህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንተንም ሆነ የቤተሰብህን አባላት ልብ ብሎ እንደሚመለከታችሁ አስተውለሃል። እሱም ለሰላምታህ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ሊያነጋግርህ እንደሚፈልግ በምልክት ጠቆመህ። ከዚያም “አንድ ነገር ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር፦ ከሌሎች ሰዎች የተለያችሁ የሆናችሁት ለምንድን ነው?” አለህ። አንተም “ጥያቄህ አልገባኝም” አልከው። ጎረቤትህ እንዲህ በማለት መለሰልህ፦ “የይሖዋ ምሥክሮች ናችሁ አይደል? እንደ ሌላው ሰው አይደላችሁም። ከሌሎች ሃይማኖቶች በጣም የተለያችሁ ናችሁ፤ ለምሳሌ በዓላትን አታከብሩም እንዲሁም በፖለቲካም ሆነ በጦርነት አትካፈሉም። ሲጋራ አታጨሱም። የቤተሰብህ አባላትም ጥሩ ሥነ ምግባር አላቸው። ይህን ያህል የተለያችሁ እንድትሆኑ ያደረጋችሁ ምንድን ነው?”

ከሌሎች የተለየን የሆንነው የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች በመሆናችን እንደሆነ ታውቃለህ። ንጉሣችን ኢየሱስ እኛን ለማጥራት ሁልጊዜ እርምጃ ይወስዳል። የእሱን ፈለግ እንድንከተልና ከዚህ ክፉ ዓለም የተለየን እንድንሆን እየረዳን ነው። መሲሐዊው መንግሥት፣ ከመንፈሳዊ ነገሮችና ከሥነ ምግባር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በድርጅታዊ አሠራር ረገድ የአምላክን ሕዝቦች ሲያጠራቸው የቆየው እንዴት እንደሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ እንመለከታለን።

በዚህ ክፍል ውስጥ . . .

ምዕራፍ 10

ንጉሡ ሕዝቦቹን በመንፈሳዊ ያጠራቸዋል

ገና እና መስቀል ምን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ?

ምዕራፍ 11

የአምላክን ቅድስና የሚያንጸባርቅ ሥነ ምግባራዊ የማጥራት ሥራ

ሕዝቅኤል በራእይ የተመለከተው ቤተ መቅደስ፣ የዘብ ቤቶች እና መግቢያዎች ከ1914 ጀምሮ ለአምላክ ሕዝቦች ልዩ ትርጉም አላቸው።

ምዕራፍ 12

‘የሰላምን አምላክ’ ለማገልገል መደራጀት

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሁከትን ያነጻጸረው ሥርዓት ከመያዝ ጋር ሳይሆን ከሰላም ጋር ነው። ለምን? የዚህ ጥያቄ መልስ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችን የሚነካው እንዴት ነው?