በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳው ይህ መጽሐፍ ‘መከራና ሥቃይ የሚደርስብን ለምንድን ነው? ስንሞት ምን እንሆናለን? ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረን ምን ማድረግ አለብን?’ ለሚሉት ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ያብራራል።

አምላክ ለእኛ ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

‘በዛሬው ጊዜ መከራ የበዛው ለምንድን ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። አምላክ በቅርቡ የሰው ልጆችን ከሥቃይ፣ ከሕመምና ከሞት እንደሚገላግላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።

ምዕራፍ 1

አምላክ ማን ነው?

አምላክ ስለ አንተ ያስባል? አምላክ ምን ባሕርያት እንዳሉትና የእሱ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ምዕራፍ 2

መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ

መጽሐፍ ቅዱስ ችግሮችህን ለመወጣት የሚረዳህ እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ላይ እምነት መጣል የምትችለው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 3

አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

በአዲስ ዓለም ውስጥ ምድር ገነት ስትሆን የሚኖረው ሕይወት ምን ይመስላል?

ምዕራፍ 4

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

ኢየሱስ አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ ነው የምንልበትን ምክንያት፣ ከየት እንደመጣ እንዲሁም የይሖዋ አንድያ ልጅ የተባለው ለምን እንደሆነ ተመልከት።

ምዕራፍ 5

ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ

ቤዛው ምንድን ነው? ለአንተስ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

ምዕራፍ 6

ስንሞት ምን እንሆናለን?

መጽሐፍ ቅዱስ የሞቱ ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ይናገራል፤ በተጨማሪም የሰው ልጆች የሚሞቱት ለምን እንደሆነ ያብራራል።

ምዕራፍ 7

የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!

የምትወደውን ሰው በሞት አጥተሃል? ዳግመኛ ልታገኘውስ ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትንሣኤ ምን እንደሚያስተምር ተመልከት።

ምዕራፍ 8

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች አቡነ ዘበሰማያት ወይም አባታችን ሆይ በመባል የሚታወቀውን ጸሎት ያውቁታል። “መንግሥትህ ይምጣ” ሲባል ምን ማለት ነው?

ምዕራፍ 9

የዓለም መጨረሻ ቀርቧል?

በዘመናችን የሚኖሩ ሰዎች ድርጊትና ባሕርይ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ እንደምንኖር የሚያረጋግጠው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ምዕራፍ 10

መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክትና ስለ አጋንንት ይናገራል። እነዚህ መንፈሳዊ ፍጡራን በእርግጥ አሉ? ሊረዱን ወይም ሊጎዱን ይችላሉ?

ምዕራፍ 11

መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?

በርካታ ሰዎች በዓለም ላይ ለሚደርሰው መከራ ተጠያቂው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ ምን ትላለህ? በሰው ልጆች ላይ መከራ የሚደርሰው ለምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ማብራሪያ ተመልከት።

ምዕራፍ 12

የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋን በሚያስደስት መንገድ መኖር ይቻላል። እንዲያውም የእሱ ወዳጅ መሆን ትችላለህ።

ምዕራፍ 13

አምላክ ለሰጠህ ሕይወት አድናቆት ይኑርህ

አምላክ ፅንስ ማስወረድን፣ ደም መውሰድንና የእንስሳን ሕይወት በተመለከተ ምን አመለካከት አለው?

ምዕራፍ 14

ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

ባሎች፣ ሚስቶች፣ ወላጆች እንዲሁም ልጆች ኢየሱስ ፍቅር በማሳየት ረገድ የተወውን ምሳሌ መከተል ይችላሉ። ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

ምዕራፍ 15

እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ማወቅ የሚቻለው እንዴት ነው?

እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ለማወቅ የሚረዱህን ስድስት ነጥቦች ተመልከት።

ምዕራፍ 16

አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ

ስለምታምንበት ነገር ለሌሎች ስትናገር ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ? ሌሎችን ቅር በማያሰኝ መንገድ እምነትህን ማስረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 17

ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት

አምላክ ጸሎትህን ይሰማል? የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ምን እንደሚያስተምር ማወቅ ያስፈልግሃል።

ምዕራፍ 18

ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል?

አንድ ሰው ለጥምቀት ብቁ እንዲሆን ምን እርምጃዎች መውሰድ አለበት? ጥምቀት ምን እንደሚያመለክት እንዲሁም እንዴት መከናወን እንዳለበት ተመልከት።

ምዕራፍ 19

ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር

አምላክ ላደረገልን በርካታ ነገሮች አድናቆት እንዳለንና አመስጋኝ እንደሆንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሐሳብ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? በተባለው መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ቃላትና ሐረጎች ትርጉም።