በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ወደ ይሖዋ ተመለስ

መደምደሚያ

መደምደሚያ

ከይሖዋ ሕዝቦች ጋር ስላሳለፍካቸው አስደሳች ጊዜያት መለስ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ለምሳሌ በጉባኤ ስብሰባ ላይ የሰማኸው አበረታች ንግግር፣ የታነጽክበት ትልቅ ስብሰባ፣ በአገልግሎት ላይ ያጋጠመህ አስደሳች ተሞክሮ ወይም ከአንድ የእምነት ባልንጀራህ ጋር ያደረግከው ግሩም ውይይት ትዝ ይልሃል? ይሖዋን እንዳልረሳኸው ግልጽ ነው፤ እሱም ቢሆን አልረሳህም። ለእሱ ታማኝ ሆነህ ያከናወንከውን አገልግሎት ምንጊዜም ያስታውሳል። ወደ እሱ እንድትመለስ ሊረዳህም ይጓጓል።

ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ። የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ። . . . ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።” —ሕዝቅኤል 34:11, 12