በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ከአምላክ የተላከ ምሥራች!

 ትምህርት 3

ምሥራቹ በእርግጥ ከአምላክ የመጣ ነው?

ምሥራቹ በእርግጥ ከአምላክ የመጣ ነው?

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?

ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም እንደሚኖሩ የሚገልጸው ምሥራች የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። (መዝሙር 37:29) መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ 66 ትናንሽ መጻሕፍትን የያዘ መጽሐፍ ነው። አምላክ እነዚህን መጻሕፍት ለማስጻፍ 40 በሚያህሉ ታማኝ ሰዎች ተጠቅሟል። ከዛሬ 3,500 ዓመታት ገደማ በፊት የመጀመሪያዎቹን አምስት መጻሕፍት የጻፈው ሙሴ ነው። የመጨረሻው መጽሐፍ የተዘጋጀው ደግሞ ከ1,900 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ሲሆን የጻፈው ሐዋርያው ዮሐንስ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ያሰፈሩት የማንን ሐሳብ ነው? አምላክ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ሐሳቡን ለጸሐፊዎቹ ገልጾላቸዋል። (2 ሳሙኤል 23:2) በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የጻፉት የራሳቸውን ሳይሆን የአምላክን ሐሳብ ነው። ስለሆነም የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት አምላክ ነው።​—2 ጢሞቴዎስ 3:16ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21ን አንብብ።

2. መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት ስለሚፈጸሙት ዝርዝር ነገሮች በትክክል ስለሚናገር ከአምላክ የመጣ መሆኑን እርግጠኞች ነን። ማንም ሰው ስለ ወደፊቱ ጊዜ በትክክል መናገር አይችልም። (ኢያሱ 23:14) ስለ ሰው ዘር የወደፊት ሕይወት በትክክል ሊተነብይ የሚችለው ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ብቻ ነው።​—ኢሳይያስ 42:9ን እና 46:10ን አንብብ።

አምላክ ያስጻፈው መጽሐፍ ከሌሎች መጻሕፍት የተለየ እንደሚሆን የሚጠበቅ ነው፤ ደግሞም የተለየ ነው። በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ተሠራጭተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ጥንት የተጻፈ መጽሐፍ ቢሆንም ከትክክለኛ ሳይንስ ጋር ይስማማል። ከዚህም ሌላ በ40 ሰዎች ቢጻፍም ሐሳቡ እርስ በርሱ አይጋጭም። * በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ አፍቃሪ እንደሆነ ፈጽሞ በማያሻማ መንገድ ይገልጻል። እንዲሁም በዛሬው ጊዜም ቢሆን ሰዎች አኗኗራቸውን አስተካክለው  የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ የማድረግ ኃይል አለው። እነዚህ እውነታዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነ እንዲያምኑ አድርገዋቸዋል።​—1 ተሰሎንቄ 2:13ን አንብብ።

3. መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ከያዛቸው መልእክቶች አንዱ አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ ለሰው ልጆች ስላደረገው ዝግጅት የሚገልጽ ምሥራች ነው። በሰው ዘር ታሪክ መጀመሪያ ላይ፣ የሰው ልጆች ገነት በሆነች ምድር ላይ የመኖር መብታቸውን እንዴት እንዳጡና ከጊዜ በኋላ ምድር እንደገና ገነት የምትሆነው እንዴት እንደሆነ ቅዱሳን መጻሕፍት ያብራራሉ።​—ራእይ 21:4, 5ን አንብብ።

ከዚህም ሌላ የአምላክ ቃል ሕጎችን፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችንና ምክሮችን ይዟል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር ስለነበረው ግንኙነት የሚገልጽ ሲሆን ይህም ስለ ባሕርያቱ ለማወቅ ያስችለናል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ እንድታውቅ ሊረዳህ ይችላል። የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነም ያብራራል።​—መዝሙር 19:7, 11ን፣ ያዕቆብ 2:23ን እና 4:8ን አንብብ

4. መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ኢየሱስ የተለያዩ ጥቅሶችን በመጥቀስ “የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም” ያብራራ ነበር። ይህ ብሮሹርም ተመሳሳይ ዘዴ በመጠቀም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እንድታውቅ ይረዳሃል።​—ሉቃስ 24:27, 45ን አንብብ።

ከአምላክ የተላከውን ምሥራች ያህል ደስታ የሚያስገኝ ነገር የለም ማለት ይቻላል። ይሁንና አንዳንድ ሰዎች ለዚህ መልእክት ግድ የላቸውም፤ ሌሎች ደግሞ ይህ መልእክት ያበሳጫቸው ይሆናል። ሆኖም ይህ ሁኔታ ተስፋ ቆርጠህ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን እንድታቆም ሊያደርግህ አይገባም። የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋህ የተመካው ስለ አምላክ እውቀት በመቅሰምህ ላይ ነው።​—ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።

 

^ አን.3 ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር ተመልከት።