በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?

የክፍል 8 ማስተዋወቂያ

የክፍል 8 ማስተዋወቂያ

ይሖዋ ሰለሞንን ታላቅ ጥበብ በመስጠት ባረከው፤ ቤተ መቅደሱን የመገንባት መብትም ሰጠው። ሰለሞን ግን ከጊዜ በኋላ ይሖዋን ተወ። ወላጅ ከሆንክ፣ የሐሰት አምልኮ ተከታዮች ሰለሞንን ከአምላክ እንዲርቅ ያደረጉት እንዴት እንደሆነ ለልጅህ አስረዳው። ከሰለሞን የግዛት ዘመን በኋላ የእስራኤል መንግሥት ተከፈለ፤ ከዚያ በኋላ የተነሱት መጥፎ ነገሥታት ሕዝቡ ከሃዲ እንዲሆንና ጣዖት እንዲያመልክ አደረጉት። በዚህ ወቅት በርካታ የይሖዋ ታማኝ ነቢያት ስደት ደርሶባቸዋል፤ እንዲሁም ተገድለዋል። ንግሥት ኤልዛቤል ደግሞ በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ውስጥ ክህደት ይበልጥ እንዲስፋፋ አደረገች። ይህ ዘመን በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ብዙ መጥፎ ነገሮች የተፈጸሙበት ወቅት ነው። ሆኖም በዚህ ጊዜም ቢሆን በእስራኤላውያን መካከል እንደ ንጉሥ ኢዮሳፍጥና ነቢዩ ኤልያስ ያሉ ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግሉ ሰዎች ነበሩ።

በዚህ ክፍል ውስጥ . . .

ትምህርት 44

የይሖዋ ቤተ መቅደስ

ይሖዋ የንጉሥ ሰለሞንን ጥያቄ በመቀበል ባርኮታል።

ትምህርት 45

የእስራኤል መንግሥት ተከፈለ

ብዙ እስራኤላውያን ይሖዋን ማገልገል አቆሙ።

ትምህርት 46

ይሖዋ እውነተኛ አምላክ መሆኑን አሳየ

እውነተኛው አምላክ ማን ነው? ይሖዋ ወይስ ባአል?

ትምህርት 47

ይሖዋ ኤልያስን አበረታታው

ይሖዋ አንተንም ሊያበረታታህ እንደሚችል ትተማመናለህ?

ትምህርት 48

የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ

በአንድ ቤት ውስጥ ሁለት ተአምር ተፈጸመ!

ትምህርት 49

ክፉዋ ንግሥት ተቀጣች

ኤልዛቤል ናቡቴን በማስገደል የወይን እርሻውን ወሰደች። ይሖዋ ግን የፈጸመችውን ክፋት ተመልክቶ ነበር።

ትምህርት 50

ይሖዋ ኢዮሳፍጥን ከጠላቶቹ አዳነው

ጥሩው ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ ጠላቶቹ ይሁዳን ለመውጋት ሲመጡ እርዳታ ለማግኘት ወደ አምላክ ጸለየ።