በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?

የክፍል 6 ማስተዋወቂያ

የክፍል 6 ማስተዋወቂያ

እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ የማደሪያው ድንኳን የእውነተኛው አምልኮ ማዕከል ሆኖ ነበር። ካህናት ሕጉን ያስተምሩ፣ መሳፍንት ደግሞ ሕዝቡን ይመሩ ነበር። ይህ ክፍል አንድ ሰው የሚወስነው ውሳኔና የሚያደርገው ነገር በሌሎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ያብራራል። እያንዳንዱ እስራኤላዊ በግለሰብ ደረጃ ለይሖዋም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ታማኝ መሆን ይጠበቅበት ነበር። ዲቦራ፣ ናኦሚ፣ ኢያሱ፣ ሐና፣ የዮፍታሔ ልጅና ሳሙኤል በሕዝባቸው ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ አሳድረው እንደነበር አብራራ። እንደ ረዓብ፣ ሩት፣ ኢያዔልና ገባዖናውያን ያሉ እስራኤላዊ ያልሆኑ ሰዎችም እንኳ አምላክ ከእስራኤላውያን ጋር እንደሆነ በማወቃቸው ከእነሱ ጎን ለመቆም እንደወሰኑ ጎላ አድርገህ ግለጽ።

በዚህ ክፍል ውስጥ . . .

ትምህርት 29

ይሖዋ ኢያሱን መረጠው

አምላክ ለኢያሱ የሰጠው መመሪያ በዛሬው ጊዜ የምንኖረውን እኛንም ይጠቅመናል።

ትምህርት 30

ረዓብ ሰላዮቹን ደበቀች

የኢያሪኮ አጥር ፈረሰ። የረዓብ ቤት የተሠራው ከአጥሩ ጋር ተያይዞ ቢሆንም እንኳ አልፈረሰም።

ትምህርት 31

ኢያሱና ገባኦናውያን

ኢያሱ ‘ፀሐይ ትቁም’ ብሎ አምላክን ለመነ። አምላክ ጸሎቱን መልሶለት ይሆን?

ትምህርት 32

አዲሱ መሪና ሁለቱ ደፋር ሴቶች

ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን ጣዖት ማምለክ ጀመሩ። በዚህ የተነሳ ችግር ገጥሟቸው የነበረ ቢሆንም በመስፍኑ ባርቅ፣ በነቢይቱ ዲቦራና በኢያዔል አማካኝነት እርዳታ አገኙ።

ትምህርት 33

ሩትና ናኦሚ

ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሁለት ሴቶች ወደ እስራኤል ተመለሱ። አንደኛዋ ሴት ማለትም ሩት በእርሻ ላይ ለመሥራት ስትሄድ ቦዔዝ ተመለከታት።

ትምህርት 34

ጌድዮን ምድያማውያንን አሸነፈ

እስራኤላውያን፣ ምድያማውያን ሲያሠቃዩአቸው እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ጮኹ። የጌድዮን ጥቂት ወታደሮች 135,000ዎቹን የጠላት ወታደሮች ያሸነፉት እንዴት ነው?

ትምህርት 35

ሐና ልጅ ለማግኘት ጸለየች

ሕልቃና ሐናን፣ ፍናናንና ልጆቹን ይዞ በሴሎ በሚገኘው የማደሪያ ድንኳን ይሖዋን ለማምለክ ሄደ። በዚያም ሐና ልጅ ለማግኘት ጸለየች። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳሙኤልን ወለደች!

ትምህርት 36

ዮፍታሔ የገባው ቃል

ዮፍታሔ ምን ቃል ገባ? ለምንስ? የዮፍታሔ ልጅ አባቷ ስለገባው ቃል ስትሰማ ምን አደረገች?

ትምህርት 37

ይሖዋ ሳሙኤልን አነጋገረው

የሊቀ ካህናቱ የኤሊ ሁለት ልጆች በማደሪያው ድንኳን ካህናት ሆነው ያገለግሉ የነበረ ቢሆንም የአምላክን ሕግ አልታዘዙም። ትንሹ ሳሙኤል ግን ከእነሱ የተለየ ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ አነጋገረው።

ትምህርት 38

ይሖዋ ለሳምሶን ታላቅ ኃይል ሰጠው

ይሖዋ፣ ሳምሶን ከፍልስጤማውያን ጋር እንዲዋጋ ሲል ኃይል ሰጠው፤ ሳምሶን የተሳሳተ ውሳኔ ሲያደርግ ግን ፍልስጤማውያን ያዙት።