በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?

 ትምህርት 76

ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

በ30 ዓ.ም. በሚያዝያ ወር አካባቢ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። ብዙ ሰዎች ፋሲካን ለማክበር ወደ ከተማዋ መጥተው ነበር። በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ሰዎች በቤተ መቅደሱ ውስጥ የእንስሳት መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ከሚኖሩበት ቦታ እንስሳት ይዘው ይመጡ ነበር፤ ሌሎቹ ደግሞ እንስሳቱን ከኢየሩሳሌም ይገዙ ነበር።

ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲገባ በዚያ እንስሳት የሚሸጡ ሰዎችን አየ። ይሖዋ በሚመለክበት ቤት ውስጥ ንግድ ጀምረው ነበር። ታዲያ ኢየሱስ ይህን ሲያይ ምን አደረገ? በገመድ ጅራፍ ሠርቶ በጎቹንና ከብቶቹን ከቤተ መቅደሱ አስወጣ። ከዚያም የገንዘብ መንዛሪዎቹን ጠረጴዛ በመገለባበጥ ሳንቲሞቻቸውን መሬት ላይ በተነ።  ርግብ የሚሸጡትንም ሰዎች ‘እነዚህን ከዚህ አውጡ! የአባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት!’ አላቸው።

በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ኢየሱስ ባደረገው ነገር ተገረሙ። ደቀ መዛሙርቱም ስለ መሲሑ የተነገረውን ‘ለይሖዋ ቤት ከፍተኛ ቅንዓት አለኝ’ የሚለውን ትንቢት አስታወሱ።

ከጊዜ በኋላም በ33 ዓ.ም. ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚነግዱትን ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ አባሯል። ለአባቱ ቤት ንቀት በሚያሳዩ ሰዎች ላይ እርምጃ ወስዷል።

“ለአምላክም ለሀብትም በአንድ ጊዜ ባሪያ መሆን አትችሉም።”—ሉቃስ 16:13