በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በተለያዩ ዘመናት የተከናወኑ ነገሮችን እንመለከታለን፤ ከእነዚህም መካከል ስለ ፍጥረት የሚናገረው ዘገባ፣ ስለ ኢየሱስ መወለድና ስላከናወነው አገልግሎት የሚገልጸው ታሪክ እንዲሁም የአምላክ መንግሥት ስለሚያመጣቸው በረከቶች የሚናገረው ዘገባ ይገኙበታል።

የበላይ አካሉ መልእክት

ይህን መጽሐፍ እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን?

ትምህርት 1

አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ ይናገራል። አምላክ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ከመፍጠሩ በፊት አንድ መልአክ የፈጠረው ለምንድን ነው?

ትምህርት 2

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ከፈጠረ በኋላ በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጣቸው። ቤተሰብ መሥርተው መላዋን ምድር ገነት እንዲያደርጉ ፈልጎ ነበር።

ትምህርት 3

አዳምና ሔዋን አምላክን ሳይታዘዙ ቀሩ

በኤደን የአትክልት ስፍራ ውስጥ የነበረው አንድ ዛፍ ከሌሎቹ የተለየ ነበር የምንለው ለምንድን ነው? ሔዋን የዚህን ዛፍ ፍሬ የበላችው ለምንድን ነው?

ትምህርት 4

ቃየን ተናዶ ወንድሙን ገደለው

አምላክ የአቤልን መባ ሲቀበል የቃየንን ግን አልተቀበለም። ቃየን ይህን ሲያውቅ በጣም ስለተናደደ መጥፎ ነገር አደረገ።

ትምህርት 5

የኖኅ መርከብ

ክፉ መላእክት በምድር ላይ የሚኖሩ ሴቶችን አግብተው ግዙፍና ጉልበተኛ የሆኑ ልጆችን ወለዱ። በሁሉም ቦታ ዓመፅ ተስፋፍቶ ነበር። ኖኅ ግን ከሌሎቹ የተለየ ነበር፤ አምላክን ይወድና ይታዘዝ ነበር።

ትምህርት 6

ስምንት ሰዎች ከጥፋት ውኃው ተረፉ

አምላክ በኖኅ ዘመን የነበረውን ዓለም ለማጥፋት 40 ቀንና 40 ሌሊት እንዲዘንብ አደረገ። ኖኅና ቤተሰቡ ከአንድ ዓመት በላይ በመርከቡ ውስጥ ቆዩ። በመጨረሻም መውጣት ቻሉ።

ትምህርት 7

የባቤል ግንብ

አንዳንድ ሰዎች ከተማ ለመገንባትና ሰማይ የሚደርስ ግንብ ለመሥራት አስበው ነበር። ይሖዋ የተለያየ ቋንቋ እንዲናገሩ ያደረጋቸው ለምንድን ነው?

ትምህርት 8

አብርሃምና ሣራ አምላክን ታዘዋል

አብርሃምና ሣራ በዑር ከተማ የነበራቸውን ሕይወት ትተው በከነአን ምድር ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑት ለምንድን ነው?

ትምህርት 9

በመጨረሻ ልጅ ወለዱ!

አምላክ ለአብርሃም የገባለትን ቃል የሚፈጽመው እንዴት ነው? ቃሉ የሚፈጸመው በይስሐቅ በኩል ነው ወይስ በእስማኤል?

ትምህርት 10

የሎጥን ሚስት አስታውሱ

አምላክ በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትና ድኝ አዘነበ። እነዚህ ከተሞች የጠፉት ለምንድን ነው? የሎጥን ሚስት ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?

ትምህርት 11

የአብርሃም እምነት ተፈተነ

አምላክ አብርሃምን ‘እባክህ አንድ ልጅህን ወስደህ በሞሪያ ምድር በሚገኝ ተራራ ላይ መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው’ አለው። አብርሃም ይህን የእምነት ፈተና እንዴት ይወጣው ይሆን?

ትምህርት 12

ያዕቆብ ውርስ አገኘ

ይስሐቅና ርብቃ፣ ኤሳውና ያዕቆብ የሚባሉ መንታ ልጆች ነበሯቸው። መጀመሪያ የተወለደው ኤሳው ስለነበር ለየት ያለ ውርስ የሚያገኘው እሱ ነበር። ለአንድ ሳህን ወጥ ሲል ይህን ውርስ አሳልፎ የሰጠው ለምንድን ነው?

ትምህርት 13

ያዕቆብና ኤሳው ታረቁ

ያዕቆብ በረከት ያገኘው እንዴት ነው? ከኤሳው ጋር የታረቀውስ እንዴት ነው?

ትምህርት 14

አምላክን የታዘዘ ባሪያ

ዮሴፍ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ ሆኖም ከባድ መከራ ደርሶበታል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርት 15

ይሖዋ ዮሴፍን አልረሳውም

ዮሴፍ ከቤተሰቡ በጣም ርቆ ይገኝ የነበረ ቢሆንም አምላክ አልተለየውም።

ትምህርት 16

ኢዮብ ማን ነበር?

ችግሮች ቢደርሱበትም ይሖዋን ታዟል።

ትምህርት 17

ሙሴ ይሖዋን ለማምለክ መረጠ

ሙሴ ሕፃን በነበረበት ወቅት እናቱ በዘዴ ሕይወቱን አትርፋለች።

ትምህርት 18

በእሳት የተያያዘው ቁጥቋጦ

እሳቱ ቁጥቋጦውን ያላቃጠለው ለምንድን ነው?

ትምህርት 19

የመጀመሪያዎቹ ሦስት መቅሰፍቶች

ትዕቢተኛ የነበረው ፈርዖን አምላክ ያዘዘውን ቀላል ነገር ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆኑ በሕዝቡ ላይ መከራ እንዲመጣ አድርጓል።

ትምህርት 20

ስድስቱ መቅሰፍቶች

እነዚህ መቅሰፍቶች ከመጀመሪያዎቹ ሦስት መቅሰፍቶች የሚለዩት በምንድን ነው?

ትምህርት 21

አሥረኛው መቅሰፍት

ይህ መቅሰፍት በጣም አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ ትዕቢተኛው ፈርዖን እንኳ ሕዝቡን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሆኗል።

ትምህርት 22

በቀይ ባሕር የተፈጸመው ተአምር

ፈርዖን ከአሥሩ መቅሰፍቶች መትረፍ የቻለ ቢሆንም ከዚህኛው የአምላክ ተአምር ማምለጥ ይችል ይሆን?

ትምህርት 23

እስራኤላውያን ለይሖዋ ቃል ገቡ

እስራኤላውያን በሲና ተራራ አቅራቢያ በሰፈሩበት ወቅት ለይሖዋ ቃል ገብተው ነበር።

ትምህርት 24

ቃላቸውን አልጠበቁም

ሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት እየተቀበለ በነበረበት ወቅት ሕዝቡ ከባድ ኃጢአት ፈጸመ።

ትምህርት 25

ለአምልኮ የሚያገለግል የማደሪያ ድንኳን

በዚህ ልዩ ድንኳን ውስጥ የቃል ኪዳኑ ታቦት ይቀመጥ ነበር።

ትምህርት 26

አሥራ ሁለቱ ሰላዮች

ኢያሱና ካሌብ የከነአንን ምድር ከሰለሉት ሌሎች አሥር ሰላዮች የተለዩ ነበሩ።

ትምህርት 27

በይሖዋ ላይ ዓመፁ

ቆሬ፣ ዳታን፣ አቤሮንና ሌሎች 250 ሰዎች ይሖዋን በተመለከተ ያላስተዋሉት አንድ ትልቅ እውነታ ነበር።

ትምህርት 28

የበለዓም አህያ ተናገረች

አህያዋ በለዓም ማየት ያልቻለውን መልአክ አየች።

ትምህርት 29

ይሖዋ ኢያሱን መረጠው

አምላክ ለኢያሱ የሰጠው መመሪያ በዛሬው ጊዜ የምንኖረውን እኛንም ይጠቅመናል።

ትምህርት 30

ረዓብ ሰላዮቹን ደበቀች

የኢያሪኮ አጥር ፈረሰ። የረዓብ ቤት የተሠራው ከአጥሩ ጋር ተያይዞ ቢሆንም እንኳ አልፈረሰም።

ትምህርት 31

ኢያሱና ገባኦናውያን

ኢያሱ ‘ፀሐይ ትቁም’ ብሎ አምላክን ለመነ። አምላክ ጸሎቱን መልሶለት ይሆን?

ትምህርት 32

አዲሱ መሪና ሁለቱ ደፋር ሴቶች

ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን ጣዖት ማምለክ ጀመሩ። በዚህ የተነሳ ችግር ገጥሟቸው የነበረ ቢሆንም በመስፍኑ ባርቅ፣ በነቢይቱ ዲቦራና በኢያዔል አማካኝነት እርዳታ አገኙ።

ትምህርት 33

ሩትና ናኦሚ

ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሁለት ሴቶች ወደ እስራኤል ተመለሱ። አንደኛዋ ሴት ማለትም ሩት በእርሻ ላይ ለመሥራት ስትሄድ ቦዔዝ ተመለከታት።

ትምህርት 34

ጌድዮን ምድያማውያንን አሸነፈ

እስራኤላውያን፣ ምድያማውያን ሲያሠቃዩአቸው እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ጮኹ። የጌድዮን ጥቂት ወታደሮች 135,000ዎቹን የጠላት ወታደሮች ያሸነፉት እንዴት ነው?

ትምህርት 35

ሐና ልጅ ለማግኘት ጸለየች

ሕልቃና ሐናን፣ ፍናናንና ልጆቹን ይዞ በሴሎ በሚገኘው የማደሪያ ድንኳን ይሖዋን ለማምለክ ሄደ። በዚያም ሐና ልጅ ለማግኘት ጸለየች። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳሙኤልን ወለደች!

ትምህርት 36

ዮፍታሔ የገባው ቃል

ዮፍታሔ ምን ቃል ገባ? ለምንስ? የዮፍታሔ ልጅ አባቷ ስለገባው ቃል ስትሰማ ምን አደረገች?

ትምህርት 37

ይሖዋ ሳሙኤልን አነጋገረው

የሊቀ ካህናቱ የኤሊ ሁለት ልጆች በማደሪያው ድንኳን ካህናት ሆነው ያገለግሉ የነበረ ቢሆንም የአምላክን ሕግ አልታዘዙም። ትንሹ ሳሙኤል ግን ከእነሱ የተለየ ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ አነጋገረው።

ትምህርት 38

ይሖዋ ለሳምሶን ታላቅ ኃይል ሰጠው

ይሖዋ፣ ሳምሶን ከፍልስጤማውያን ጋር እንዲዋጋ ሲል ኃይል ሰጠው፤ ሳምሶን የተሳሳተ ውሳኔ ሲያደርግ ግን ፍልስጤማውያን ያዙት።

ትምህርት 39

የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ

አምላክ ለእስራኤላውያን የሚመሯቸው መሳፍንት ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲሾምላቸው ፈለጉ። ሳሙኤል ሳኦልን የመጀመሪያው ንጉሥ እንዲሆን ቀባው፤ በኋላ ግን ይሖዋ ሳኦልን ትቶ ሌላ ንጉሥ ለመሾም ወሰነ። ለምን?

ትምህርት 40

ዳዊት እና ጎልያድ

ይሖዋ ቀጣዩ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መረጠው፤ ዳዊት ያደረገው ነገር እሱ ንጉሥ እንዲሆን መመረጡ ተገቢ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ትምህርት 41

ዳዊት እና ሳኦል

ሳኦል ዳዊትን የጠላው ለምንድን ነው? ዳዊትስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ትምህርት  42

ዮናታን ደፋርና ታማኝ ነበር

የንጉሡ ልጅ የዳዊት ጓደኛ ሆነ።

ትምህርት 43

ንጉሥ ዳዊት የሠራው ኃጢአት

ዳዊት ያደረገው መጥፎ ውሳኔ ብዙ ችግር አስከትሏል።

ትምህርት 44

የይሖዋ ቤተ መቅደስ

ይሖዋ የንጉሥ ሰለሞንን ጥያቄ በመቀበል ባርኮታል።

ትምህርት 45

የእስራኤል መንግሥት ተከፈለ

ብዙ እስራኤላውያን ይሖዋን ማገልገል አቆሙ።

ትምህርት 46

ይሖዋ እውነተኛ አምላክ መሆኑን አሳየ

እውነተኛው አምላክ ማን ነው? ይሖዋ ወይስ ባአል?

ትምህርት 47

ይሖዋ ኤልያስን አበረታታው

ይሖዋ አንተንም ሊያበረታታህ እንደሚችል ትተማመናለህ?

ትምህርት 48

የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ

በአንድ ቤት ውስጥ ሁለት ተአምር ተፈጸመ!

ትምህርት 49

ክፉዋ ንግሥት ተቀጣች

ኤልዛቤል ናቡቴን በማስገደል የወይን እርሻውን ወሰደች። ይሖዋ ግን የፈጸመችውን ክፋት ተመልክቶ ነበር።

ትምህርት 50

ይሖዋ ኢዮሳፍጥን ከጠላቶቹ አዳነው

ጥሩው ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ ጠላቶቹ ይሁዳን ለመውጋት ሲመጡ እርዳታ ለማግኘት ወደ አምላክ ጸለየ።

ትምህርት 51

የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ

አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ ይሖዋ ስላለው ታላቅ ኃይል ለእመቤቷ ነገረቻት፤ ይህም አስገራሚ ውጤት አስገኘ።

ትምህርት 52

የይሖዋ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች

የኤልሳዕ አገልጋይ፣ ኤልሳዕ ‘ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ’ ያለው ለምን እንደሆነ ማስተዋል ቻለ።

ትምህርት 53

ዮዳሄ ያሳየው ድፍረት

አንድ ታማኝ ካህን አንዲትን ክፉ ንግሥት ተቃወማት።

ትምህርት 54

ይሖዋ ዮናስን በትዕግሥት አስተማረው

አንድ የአምላክ ነቢይ በትልቅ ዓሣ የተዋጠው ለምንድን ነው? ከዓሣው ሆድ የወጣውስ እንዴት ነው? ይሖዋ ዮናስን ምን አስተማረው?

ትምህርት 55

የይሖዋ መልአክ ሕዝቅያስን አዳነው

የይሁዳ ጠላቶች ይሖዋ ሕዝቡን አይጠብቅም ብለው ነበር፤ ሆኖም ተሳስተዋል!

ትምህርት 56

ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር

ኢዮስያስ የስምንት ዓመት ልጅ ሳለ ንጉሥ ሆነ፤ ሕዝቡንም ይሖዋን እንዲያመልኩ ረዳቸው።

ትምህርት 57

ይሖዋ ኤርምያስን እንዲሰብክ ላከው

ወጣቱ ነቢይ የተናገረው ነገር የይሁዳን ሽማግሌዎች በጣም አበሳጫቸው።

ትምህርት 58

ኢየሩሳሌም ጠፋች

የይሁዳ ሕዝብ የሐሰት አማልክትን ማምለካቸውን ቀጠሉ፤ ስለዚህ ይሖዋ ተዋቸው።

ትምህርት 59

ይሖዋን የታዘዙ አራት ልጆች

አይሁዳውያን ወጣቶች በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር ቤተ መንግሥት ውስጥ በነበሩበት ጊዜም ጭምር ለይሖዋ ታማኝ ለመሆን ወስነው ነበር።

ትምህርት 60

ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር መንግሥት

ዳንኤል ናቡከደነጾር ያየው ሕልም ትርጉም ምን እንደሆነ ተናገረ።

ትምህርት 61

ለወርቁ ምስል አልሰገዱም

ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ የባቢሎን ንጉሥ ላሠራው የወርቅ ምስል ለመስገድ ፈቃደኛ አልሆኑም።

ትምህርት 62

በትልቅ ዛፍ የተመሰለ መንግሥት

ናቡከደነጾር ያየው ሕልም ወደፊት የሚገጥመውን ሁኔታ የሚገልጽ ነበር።

ትምህርት 63

በግድግዳው ላይ የታየው ጽሑፍ

ይህ ጽሑፍ የታየው መቼ ነው? ትርጉሙስ ምንድን ነው?

ትምህርት 64

ዳንኤል አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ

ልክ እንደ ዳንኤል በየቀኑ ወደ ይሖዋ ጸልይ!

ትምህርት 65

አስቴር ሕዝቧን ከጥፋት አዳነች

አስቴር ከሌላ አገር የመጣችና ወላጆቿ የሞቱባት ብትሆንም እንኳ ንግሥት ለመሆን በቅታለች።

ትምህርት 66

ዕዝራ የአምላክን ሕግ አስተማረ

እስራኤላውያን፣ ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ካነበበላቸው በኋላ ለአምላክ ቃል ገቡ።

ትምህርት 67

የኢየሩሳሌም ግንብ

ነህምያ ጠላቶቹ ጥቃት ለመሰንዘር እንዳሰቡ ቢያውቅም ያልፈራው ለምንድን ነው?

ትምህርት 68

ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች

የኤልሳቤጥ ባል ልጁ እስከሚወለድ ድረስ መናገር እንደማይችል የተነገረው ለምንድን ነው?

ትምህርት 69

ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት

ሕይወቷን የሚለውጥ አንድ መልእክት ነገራት።

ትምህርት 70

መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ተናገሩ

የኢየሱስን መወለድ የሰሙት እረኞች ፈጣን እርምጃ ወሰዱ።

ትምህርት 71

ይሖዋ ኢየሱስን ጠበቀው

አንድ ክፉ ንጉሥ ኢየሱስ እንዲገደል ፈለገ።

ትምህርት 72

ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ

ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ የነበሩትን አስተማሪዎች ያስደነቃቸው እንዴት ነው?

ትምህርት 73

ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ

ዮሐንስ ካደገ በኋላ ነቢይ ሆነ። ዮሐንስ መሲሑ እንደሚመጣ ያስተምር ነበር። ሕዝቡ ዮሐንስ ያስተማረውን ትምህርት ሲሰሙ ምን አደረጉ?

ትምህርት 74

ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

ዮሐንስ ኢየሱስን ‘የአምላክ በግ’ በማለት ሲጠራው ምን ማለቱ ነበር?

ትምህርት 75

ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው

ዲያብሎስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ፈተነው። ሦስቱ ፈተናዎች የትኞቹ ናቸው? ኢየሱስስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ትምህርት 76

ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

ኢየሱስ እንስሳቱን ከቤተ መቅደሱ ያባረረውና የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛ የገለባበጠው ለምንድን ነው?

ትምህርት 77

ውኃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊት ሴት

አንዲት ሳምራዊት ሴት ኢየሱስ ሲያነጋግራት በጣም ተገረመች። ለምን? ኢየሱስ ለሌላ ለማንም ሰው ያልተናገረውን ምን ነገር ነገራት?

ትምህርት 78

ኢየሱስ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ሰበከ

ኢየሱስ አንዳንድ ደቀ መዛሙርቱን “ሰው አጥማጆች” እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበላቸው። ከጊዜ በኋላም ከተከታዮቹ መካከል 70ዎቹን ምሥራቹን እንዲሰብኩ አሠለጠናቸው።

ትምህርት 79

ኢየሱስ ብዙ ተአምራት ፈጽሟል

ኢየሱስ በሄደበት ቦታ ሁሉ፣ የታመሙ ሰዎች ከበሽታቸው እንዲያድናቸው ወደ እሱ ይመጡ ነበር፤ እሱም ሁሉንም ፈውሷቸዋል። አንዲትን የሞተች ልጅ እንኳ አስነስቷል።

ትምህርት 80

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ

ኢየሱስ የመረጣቸው ለምንድን ነው? ስማቸውን ታስታውሳለህ?

ትምህርት 81

የተራራው ስብከት

ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ ጠቃሚ ትምህርት ሰጠ።

ትምህርት 82

ኢየሱስ ስለ ጸሎት አስተማረ

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ የትኞቹ ነገሮች ደጋግመው እንዲለምኑ ነግሯቸዋል?

ትምህርት 83

ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ

ይህ ተአምር ኢየሱስንና ይሖዋን በተመለከተ ምን ያስተምረናል?

ትምህርት 84

ኢየሱስ በውኃ ላይ ሄደ

ሐዋርያቱ ይህ ተአምር ሲፈጸም ሲያዩ ምን ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላለህ?

ትምህርት 85

ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድን ዓይነ ስውር ፈወሰ

ኢየሱስ ባደረገው ነገር አንዳንድ ሰዎች ያልተደሰቱት ለምንድን ነው?

ትምህርት 86

ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው

ኢየሱስ ማርያም ስታለቅስ ሲያይ እሱም ማልቀስ ጀመረ። ሆኖም ሐዘናቸው ወዲያውኑ በደስታ ተተካ።

ትምህርት 87

የጌታ ራት

ኢየሱስ ከሐዋርያቱ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ፋሲካን ባከበረበት ወቅት አስፈላጊ መመሪያዎች ሰጥቷቸዋል።

ትምህርት 88

ኢየሱስ ታሰረ

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን ለማስያዝ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎችን አስከትሎ መጣ።

ትምህርት 89

ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

በቀያፋ ግቢ ውስጥ ምን ሁኔታ ተፈጠረ? ኢየሱስስ በቀያፋ ቤት ውስጥ ምን ደረሰበት?

ትምህርት 90

ኢየሱስ በጎልጎታ ተገደለ

ጲላጦስ ኢየሱስ እንዲገደል ያዘዘው ለምንድን ነው?

ትምህርት 91

ኢየሱስ ከሞት ተነሳ

ኢየሱስ ከተገደለ በኋላ ባሉት ቀናት ውስጥ ምን አስደናቂ ነገሮች ተፈጸሙ?

ትምህርት 92

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ ታየ

ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን ትኩረት ለማግኘት ሲል ምን አደረገ?

ትምህርት 93

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከመውጣቱ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ አንዳንድ አስፈላጊ መመሪያዎች ሰጣቸው።

ትምህርት 94

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ

መንፈስ ቅዱስ ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ምን ተአምራዊ ችሎታ ሰጣቸው?

ትምህርት 95

ምንም ነገር ሊያስቆማቸው አልቻለም

ኢየሱስን ያስገደሉት የሃይማኖት መሪዎች ደቀ መዛሙርቱን ዝም ለማሰኘት ሞከሩ። ሆኖም አልተሳካላቸውም።

ትምህርት 96

ኢየሱስ ሳኦልን መረጠው

ሳኦል የክርስቲያኖች ቀንደኛ ጠላት ነበር፤ ሆኖም ሕይወቱን የሚለውጥ ነገር አጋጠመው።

ትምህርት 97

ቆርኔሌዎስ መንፈስ ቅዱስ ተቀበለ

አምላክ ጴጥሮስን አይሁዳዊ ወዳልሆነው ወደዚህ ሰው ቤት የላከው ለምንድን ነው?

ትምህርት 98

ክርስትና ወደ ብዙ አገሮች ተስፋፋ

ሐዋርያው ጳውሎስና የአገልግሎት ጓደኞቹ ርቀው በሚገኙ ቦታዎች መስበክ ጀመሩ።

ትምህርት 99

አንድ የእስር ቤት ጠባቂ ክርስቲያን ሆነ

ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩት ለምንድን ነው? የእስር ቤቱ ጠባቂ እውነትን የተማረው እንዴት ነው?

ትምህርት 100

ጳውሎስና ጢሞቴዎስ

ሁለቱ ሰዎች ለብዙ ዓመታት ጓደኛሞች ሆነው ኖረዋል፤ እንዲሁም ይሖዋን አብረው አገልግለዋል።

ትምህርት 101

ጳውሎስ ወደ ሮም ተወሰደ

ጉዞው በጣም አደገኛ ነበር፤ ሆኖም የትኛውም ችግር ቢሆን ይህን ሐዋርያ ሊያስቆመው አልቻለም።

ትምህርት 102

የዮሐንስ ራእይ

ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚገልጹ ራእዮችን አሳየው።

ትምህርት 103

“መንግሥትህ ይምጣ”

የዮሐንስ ራእይ የአምላክ መንግሥት ምድርን በሚገዛበት ወቅት የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት እንደሚኖራቸው ይገልጻል።