በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ

 ክፍል 6

ከታላቁ የጥፋት ውኃ ምን እንማራለን?

ከታላቁ የጥፋት ውኃ ምን እንማራለን?

አምላክ ክፉ ሰዎችን ያጠፋ ሲሆን ኖኅንና ቤተሰቡን ግን አድኗል። ዘፍጥረት 7:11, 12, 23

አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዝናብ ዘነበ፤ ምድሪቱም ሙሉ በሙሉ በውኃ ተሸፈነች። ክፉዎቹ ሰዎች በሙሉ ሞቱ።

ዓመፀኞቹ መላእክት ሥጋዊ አካላቸውን በመተው አጋንንት ሆኑ።በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ሰዎች በሕይወት ተረፉ። ኖኅና ቤተሰቡ ከጊዜ በኋላ የሞቱ ቢሆንም እንኳ አምላክ ለዘላለም እንዲኖሩ ከሞት ያስነሳቸዋል።

 አምላክ አሁንም ክፉዎችን አጥፍቶ ጥሩ ሰዎችን ያድናል። ማቴዎስ 24:37-39

ሰይጣንና አጋንንቱ ሰዎችን ማሳሳታቸውን ቀጥለዋል።

በኖኅ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ብዙ ሰዎች የይሖዋን ፍቅራዊ መመሪያ አይቀበሉም። በቅርቡ ይሖዋ ክፉ ሰዎችን ሁሉ ያጠፋል።—2 ጴጥሮስ 2:5, 6

እንደ ኖኅ ያሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። እነሱም አምላክን የሚሰሙ ሲሆን እሱ የሚለውን ያደርጋሉ፤ እነዚህ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው።