በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ

 ክፍል 7

ኢየሱስ ማን ነበር?

ኢየሱስ ማን ነበር?

ይሖዋ ኢየሱስን ወደ ምድር ላከው። 1 ዮሐንስ 4:9

ይሖዋን ለማስደሰት ከፈለግን ሌላም ልንሰማው የሚገባን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አካል አለ። ይሖዋ አዳምን ከመፍጠሩ ከረጅም ጊዜ በፊት በሰማይ አንድ ኃያል መንፈሳዊ አካል ፈጥሮ ነበር።

ከጊዜ በኋላ፣ ይሖዋ ይህ መንፈሳዊ አካል በቤተልሔም፣ ማርያም ከተባለች አንዲት ድንግል እንዲወለድ አደረገ። ልጁም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።—ዮሐንስ 6:38

ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ በኖረበት ጊዜ የአምላክን ባሕርያት ፍጹም በሆነ መንገድ አንጸባርቋል። ደግ፣ አፍቃሪና የሚቀረብ ሰው ነበር። ስለ ይሖዋ የሚናገረውን እውነት ለሌሎች በድፍረት ያስተምር ነበር።

 ኢየሱስ መልካም ነገር ያደረገ ቢሆንም ሰዎች ጠልተውት ነበር። 1 ጴጥሮስ 2:21-24

የሃይማኖት መሪዎቹ የሐሰት ትምህርቶቻቸውንና ክፉ ሥራቸውን ስለሚያጋልጥባቸው ኢየሱስን ይጠሉት ነበር።

ኢየሱስ የታመሙትን ፈውሷል፤ የሞቱ ሰዎችንም አስነስቷል።

የሃይማኖት መሪዎቹ ሮማውያንን በማሳመን ኢየሱስን እንዲደበድቡትና እንዲገድሉት አደረጉ።