በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ

 ክፍል 4

ሰይጣንን መስማታቸው ምን ውጤት አስከተለ?

ሰይጣንን መስማታቸው ምን ውጤት አስከተለ?

አዳምና ሔዋን አምላክን አልታዘዙም፤ በዚህም ምክንያት ሞቱ። ዘፍጥረት 3:6, 23

ሔዋን እባቡ የነገራትን ሰምታ ፍሬውን በላች። ከዚያም ለአዳም ሰጠችው፤ እሱም በላ።

የሠሩት ነገር ስህተት ይኸውም ኃጢአት ነበር። አምላክ መኖሪያቸው ከነበረችው ገነት እንዲባረሩ አደረገ።

የእነሱም ሆነ የልጆቻቸው ሕይወት በችግር የተሞላ ሆነ። በኋላም አርጅተው ሞቱ። ወደ መንፈሳዊው ዓለም አልሄዱም፤ ከዚህ ይልቅ ከሕልውና ውጭ ሆኑ።

 የሞቱ ሰዎች ልክ እንደ አፈር ሕይወት አልባ ናቸው። ዘፍጥረት 3:19

ሁላችንም የአዳምና የሔዋን ልጆች ስለሆንን እንሞታለን። ሙታን ማየት፣ መስማትም ሆነ ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም።—መክብብ 9:5, 10

ይሖዋ ሰዎች እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። በሞት ያንቀላፉትን ሰዎች ሁሉ በቅርቡ ዳግመኛ ሕያው ያደርጋቸዋል። እሱን የሚሰሙት ከሆነ ለዘላለም ይኖራሉ።