በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ

 ክፍል 10

አምላክን የሚሰሙ ሰዎች ምን በረከቶች ይጠብቋቸዋል?

አምላክን የሚሰሙ ሰዎች ምን በረከቶች ይጠብቋቸዋል?

ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ እንደገና በምድር ላይ በሕይወት ለመኖር ከሞት ይነሳሉ። የሐዋርያት ሥራ 24:15

ይሖዋ የሚለውን የምትሰማ ከሆነ ወደፊት ምን በረከቶችን እንደምታገኝ እስቲ አስብ! የተሟላ ጤንነት ይኖርሃል፤ ሕመምተኛም ሆነ አቅመ ደካማ ሰው አይኖርም። ክፉ ሰዎች አይኖሩም፤ በመሆኑም የምትጠራጠረው አንድም ሰው አይኖርም።

ሥቃይ፣ ሐዘንም ሆነ ለቅሶ አይኖርም። ማንም ሰው አያረጅም እንዲሁም አይሞትም።

 በወዳጆችህና በቤተሰቦችህ ተከበህ ትኖራለህ። በገነት ውስጥ የሚኖረው ሕይወት እጅግ አስደሳች ይሆናል።

የሚያስፈራ ነገር አይኖርም። ሰዎች እውነተኛ ደስታ ያገኛሉ።

የአምላክ መንግሥት ሥቃይንና መከራን ሁሉ ያስወግዳል። ራእይ 21:3, 4