በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 ክፍል 13

አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ከመጥፎ ነገር ራቅ። 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10

ይሖዋን የምንወደው ከሆነ እሱ የሚጠላቸውን ነገሮች አናደርግም።

ይሖዋ እንድንሰርቅ፣ እንድንሰክር ወይም አደንዛዥ ዕፆች እንድንወስድ አይፈልግም።

አምላክ ነፍስ ግድያን፣ ፅንስ ማስወረድንና ግብረ ሰዶምን ይጠላል። ከዚህም በላይ ስግብግቦች እንድንሆን ወይም ከሌሎች ጋር እንድንጣላ አይፈልግም።

ጣዖታትን ማምለክ ወይም በመናፍስታዊ ድርጊቶች መካፈል የለብንም።

መጥፎ ነገሮችን የሚፈጽሙ ሰዎች በቅርቡ በምትመጣው ምድራዊ ገነት ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም።

 መልካም የሆነውን ነገር አድርግ። ማቴዎስ 7:12

አምላክን ማስደሰት ከፈለግን እሱን ለመምሰል ጥረት ማድረግ አለብን።

ደግና ለጋስ በመሆን ለሌሎች ፍቅር አሳይ።

ሐቀኛ ሁን።

መሐሪና ይቅር ባይ ሁን።

ስለ ይሖዋና ስለ መንገዶቹ ለሌሎች ተናገር።—ኢሳይያስ 43:10