በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ

 ክፍል 9

ምድር ገነት የምትሆነው መቼ ነው?

ምድር ገነት የምትሆነው መቼ ነው?

በምድር ላይ ያሉት ችግሮች የአምላክ መንግሥት በቅርቡ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳያሉ። ሉቃስ 21:10, 11 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ እየተከናወኑ ያሉት ነገሮች እንደሚፈጸሙ አስቀድሞ ተናግሯል። ሰዎች ገንዘብን የሚወዱ፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ ጨካኞችና ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ እንደሚሆኑ ተናግሯል።

ታላላቅ የምድር ነውጦች፣ ጦርነቶች፣ የምግብ እጥረትና ወረርሽኝ በሽታዎች እንደሚከሰቱ ገልጿል። እነዚህ ነገሮች በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸሙ ነው።

በተጨማሪም ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸው ምሥራች በመላው ምድር እንደሚሰበክ ተናግሯል። —ማቴዎስ 24:14

 የአምላክ መንግሥት ክፋትን ሁሉ ያስወግዳል። 2 ጴጥሮስ 3:13

ይሖዋ በቅርቡ ክፉዎችን ሁሉ ያጠፋል።

ሰይጣንና አጋንንቱ ይቀጣሉ።

አምላክን የሚሰሙ ሰዎች ከጥፋት ተርፈው ጽድቅ ወደሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ይገባሉ፤ በዚያም ፍርሃት አይኖርም፤ በሰዎች መካከል የመተማመን መንፈስና ፍቅር ይሰፍናል።